ሀገርን ከመፍረስ ለማዳን በሚደረገው ሂደት ሁሉ የመምህራን ሚና ከፍተኛ ነው
አዲስ አበባ፣ ህዳር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከ2 ሺህ በላይ ከሚሆኑ የከተማዋ መምህራኖች ጋር በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል።
ሃገር በታሪክ በውጭ ሃይል ተወራ በልጆቿ የበረታ ክንድ ክብሯ ተጠብቆ የቆየውን ማንነት በአሁኑ ትውልድም መደገም እንዳለበት በውይይቱ ተነስቷል።
ኢትዮጵያን ትንሽ ሊያደርጉ ትንንሽ አስተሳሰብ የፈጠሩ ያሴሩት ሴራ መዳረሻ ሁሉ ውርደትን መከናነብ ነው ብለዋል የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ።
አሁንም ሃገሪቱ ከውስጥና ከውጭ የተቃጣባትን ፈተና በመወጣት ኢትዮጵያውያን ሃላፊነታችን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
በዚህ ሀገርን ከመፍረስ ለማዳን በሚደረገው ሂደት ሁሉ የመምህራኑ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም ሃላፊው አሳስበዋል።
በይስማው አደራው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን