Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓትከካሳጊታና ሙዲና ከተሞች ከመባረሩ በፊት ሕጻናትና ሴቶችን ጨፍጭፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአሸባሪው ህወሓት ወራሪ በአፋር ክልል ካሳጊታ እና ሙዲና ከተሞች በወገን ጦር ተመትቶ ከመሸሹ በፊት በርካታ ሕጻናትና ሴቶችን መጨፍጨፉ እንዲሁም ንብረት ማውደሙ ተገለጸ፡፡
በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው መላው የጸጥታ ኃይል በካሳጊታ ግንባር አሸባሪው ህወሓትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ስትራቴጂካዊ ስፍራዎችን ማስለቀቁ ይታወቃል፡፡
የጸጥታ ኃይሉ ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ መሆኑንም ትናንት ማምሻውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጹ ይታወሳል፡፡
ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለጹት÷ አሸባሪ ቡድኑ በካሳጊታ እና ሙዲና ከተሞች የወገን ጦርን መቋቋም አቅቶት ከመሸሹ በፊት በርካታ ህጻናትንና ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ አቅመ ደካሞችን ጨፍጭፏል፡፡
መስጂዶችን አውድሟል፤ ቁራዓን ሰብስቦ አቃጥሏል፡፡
የዜጎች ጥሪቶች የሆኑ ቤቶች፣ ሱቆች፣ ምግብ ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በከባድ መሳሪያ በመምታትና በእሳት በማቃጠል አውድሟል።
አሸባሪ ቡድኑ የዜጎችን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሃብታዊ መሰረተ ልማቶች በማውደም ለሰው ልጆች የማይበጅ አረመኔያዊ ቡድን መሆኑን በተግባር አረጋግጧል።
የአሸባሪው ህወሓት ወራሪ ኃይል በወገን ጦር እየደረሰበት ያለውን ምት መቋቋም አቅቶት የያዘውን ሁሉ እያዝረከረከ በመፈርጠጥ ላይ ይገኛል።
መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ሽንፈት ገጥሞት በመፈርጠጥ ላይ የሚገኘው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን እያወደመና እየዘረፈ እንዳይሄድ ህብረተሰቡ አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.