Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 61 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች 837 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል አለ የክልሉ የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ አሕመድ ኢድሪስ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አገልግሎት አሰጣጥ ምቹና…

ቤተክርስቲያኗ በመዲናዋ ለሚከናወኑ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ለሚገኙ የልማት ሥራዎች የምታደርገውን ሁሉን አቀፍ ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች አሉ ብፁዓን አባቶች፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶች…

ሁሉንም አካባቢ ያማከለ ትምህርት በፍትሐዊነት ተደራሽ ማድረግ ይገባል – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ እና የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በጋምቤላ ከተማ ሁለት ሞዴል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን አስጀምረዋል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንዳሉት፤…

በአውቶቡስ አገልግሎት ላይ የተደረገው የሰዓት ማሻሻያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በከተማ በአውቶቡስ አገልግሎት ላይ የተደረገው የሰዓት ማሻሻያ ሕብረተሰቡ አምሽቶ ሳይቸገር ወደ ቤቱ እንዲመለስ በማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የኢንተለጀንት…

ደቡብ ዕዝ ሀገራዊ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው – ሜ/ጄ አድማሱ አለሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሠራዊት ደቡብ ዕዝ ሀገራዊ ግዳጁን በብቃትና ጀግንነት እየተወጣ ነው አሉ የዕዙ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄነራል አድማሱ አለሙ፡፡ ሜጀር ጄነራል አድማሱ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ ደቡብ ዕዝ የሠራዊቱን ሁለንተናዊ የማድረግ አቅም ለማሳደግ…

የማሕበረሰብ አንቂዎችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በሀገራዊ ምክክሩ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፌደራል ተቋማትና ማህበራት የምክክር ምዕራፍ የሚሳተፉ ተፅዕኖ ፈጣሪና የማህበረሰብ አንቂ ወኪሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ተጀምሯል፡፡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ…

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 46ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች እንደሚከተለው ቀርቧል፡- 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን…

የኤም ፖክስ በሽታ እንዳይዛመት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኤም ፖክስ (Mpox) በሽታ እንዳይዛመት በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፡፡ ሚኒስትሯ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ አስተዳደር በኤም ፖክስ ከተጠረጠሩ ሰዎች በተወሰደ…

በደቡብ ጎንደር ዞን በትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ጎንደር ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው 18 ሰዎችን አሳፍሮ ከጎንደር ወደ ባሕር ዳር ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ይፋግ ንዑስ ጣቢያ አካባቢ ከቆመ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ መከሰቱን የዞኑ ፖሊስ…

107 የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት 107 የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ደንበኞች መስተንግዶ፣ ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭና ከሌሎች ልዩ ልዩ…