Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ በመመረቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ)ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በቀጣናው ብሎም በዓለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። አንቶኒዮ ጉተሬዝ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ…

በኢትዮጵያ የስፖርት ሜዳ አርቴፊሻል ሳር ለማልበስ የሚያስችል ስምምነት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የስፖርት ሜዳዎችን አርቴፊሻል ሳር ለማልበስ የሚያስችል ስምምነት ተደርጓል። በስምምነት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራ እና ሌሎች እንግዶች…

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመስከረም ወር ለሚከበሩ በዓላት ዝግጅት ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ10 ብሔረሰቦችን የዘመን መለወጫ በዓላት በጋራ ለማክበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል አለ የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ እንዳሉት ÷ በክልሉ በሚከበሩ የዘመን መለወጫ በዓላት ላይ ከ409…

በፕሬዚዳንት ታዬ የተመራ ልዑክ በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ ልዑካን ቡድን በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ኒውዮርክ ገብቷል። የልዑካን ቡድኑ አባላት አሁን ላይም 'ደህናነት በአብሮነት' በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው 80ኛው…

የጋሞ ብሔረሰብ ባሕል፣ ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚዬም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋሞ ዞን የ'ዮ ማስቃላ' በዓል አከባበር አካል የሆነው የጋሞ ብሔረሰብ የባሕል፣ ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚዬም በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡ ሲምፖዚዬሙ''ዱቡሻና ዱቡሻ ወጋ ለዘላቂ ሰላማችን እና ልማታችን'' በሚል መሪ ሃሳብ ነው…

ወላይታ ድቻ እና አል ኢትሃድ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ከአል ኢትሃድ ጋር ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል። በውድድሩ ኢትዮጵያን የሚወክለው ወላይታ ድቻ ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከሊቢያው አል ኢትሃድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በአቻ ውጤት…

የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና አገልግሎት ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና አገልግሎት ማዕከል ግንባታ ተጀምሯል። የማዕከሉን መሰረተ ድንጋይ ያስቀመጡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በወቅቱ እንዳሉት፤ መንግስት ባለፉት ዓመታት ለጤናው ዘርፍ…

የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የጀግንነት ታሪክ ዳግም በደማቅ ቀለም የተጻፈበት ነው – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‌‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የድል እና የጀግንነት ታሪክ ዳግም በደማቅ ቀለም የተጻፈበት ነውአሉ። የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቁን…

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዘመን ተሻጋሪ የስኬት ማህተም ነው – ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማንኛውንም ነገር ማሳካት እንደምንችል በተግባር ያረጋገጠ ዘመን ተሻጋሪ የስኬት ማህተም ነው አሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ። የግድቡን መጠናቀቅን በማስመልከት በጅግጅጋ ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ…

የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል የፊታችን መስከረም 24 እና 25 ቀን ይከበራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 24 ቀን በሆረ ፊንፊኔ እና መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም በሆረ ሀርሰዲ ይከበራል፡፡ የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት በሰጡት መግለጫ ÷ የኢሬቻ በዓል የምሥጋና፣ የአንድነት፣ የፍቅር እና የእርቅ በዓል መሆኑን…