Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

የጽ/ቤቱን ቼክ በማውጣት ከ17 ሚሊየን ብር በላይ በመመዝበር የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በህገወጥ መንገድ የጉለሌ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳዳር ጽ/ቤትን ቼክ በማውጣት ከ17 ሚሊየን ብር በላይ በመመዝበር በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው። በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል…

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የጋራ ጥረት ያስፈልጋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰው የመነገድና በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል አለ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ፡፡ ቢሮው በሰው የመነገድ፥ በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ድንበር የማሻገርና…

የሀይማኖት ተቋማት የሀገርን ሰላም ለማጽናት ያላቸውን ሚና ማጠናከር ይገባል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀይማኖት ተቋማት አብሮነትን በማጠናከር የሀገርን ሰላም ለማጽናት ያላቸውን ሚና ማጠናከር ይገባል አለ የሰላም ሚኒስቴር፡፡ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያዘጋጀው 4ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ "ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለአንድነትና…

በኦሮሚያ ክልል ከ7 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ህፃናትን በቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ7 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ህፃናትን በቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው። የክልሉ ቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም አስተባባሪ ታምሩ ታደሰ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ…

በኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻ የሚሆን የአግሮ ኬሚካል ግብአት እየቀረበ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻ የሚሆን የአግሮ ኬሚካል ግብአት በሁሉም ዞኖች እየቀረበ ነው አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡ በቢሮው የግብርና ግብአት ፍላጎትና አቅርቦት ዳይሬክተር አቶ ታከለ ቁሩንዲ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥…

ዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ሥነ ምሕዳርን መጠበቅ የሚያስችሉ ሥራዎችን እያከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 28፣ (ኤፍ ኤም ሲ) አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ ሀገር በቀል እፅዋትን በመጠበቅ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እየሰራሁ ነው አለ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የብዝሃ ሕይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ዳይሬክተር ሽቴ ጋተው (ዶ/ር) ÷ በመጥፋት ላይ ያሉ የእፅዋት ዝርያዎችን…

ክረምትና የከሰል ጭስ…

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ክረምቱን ተከትሎ ከሚመጣው ቅዝቃዜ ጋር ተያይዞ የሰዎች የከሰል አጠቃቀም ከወትሮው በተለየ መልኩ ይጨምራል፡፡ በርካቶች በክረምት ወቅት በቤታቸው የሚኖርን ቅዝቃዜ ለመከላከል ከሰልን ሙቀት ለመፍጠር ሲጠቀሙ በስፋት ይስተዋላል፡፡ በሌላ በኩል…

የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት በሐረር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባላት በሐረር ከተማ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ በተገነባው ኢኮ ፓርክ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እና…

ሚኒስቴሩ በየመን በጀልባ መስጠም አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን የተሰማውን ሃዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየመን በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በደረሰው የሞት አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል፡፡ ሚኒስቴሩ የደረሰውን አደጋ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እያጣራ መሆኑን ለፋና ዲጂታል…

ኢዜአ በብዝኃ ቋንቋ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካን ለዓለም ለማሳየት የያዘው ግብ የሚደነቅ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በብዝኃ ቋንቋ ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካን ለዓለም ለማሳየት የያዘው ግብ የሚደነቅ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት…