የሞጆ ደረቅ ወደብን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ማዕከል በማድረግ የሎጂስቲክስ ስራዎችን ለማሳለጥ እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞጆ ደረቅ ወደብን የአረንጓዴ አሻራ ልማት ማዕከል በማድረግ የሎጂስቲክስ ስራዎችን ለማሳለጥ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን አስታውቋል።
የማሪታይም ባለስልጣን አመራሮችና ሠራተኞች፣ የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሰራተኞች…