Fana: At a Speed of Life!

ግለሰብን አሳፍረው በመውሰድ ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል የተባሉ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መንገድ ዳር ቆማ ታክሲ በመጠበቅ ላይ የነበረችን ግለሰብ በባለሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) አሳፍረው በመውሰድ ንብረቷን ወስደው ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል የተባሉ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ፡፡ የዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው…

የሸገር ደርቢ ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በዱባይ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ በተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ዱባይ ከተማ እንደሚካሄድ ክለቦቹ አስታውቀዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ክለቦች በሰጡት መግለጫ ÷በመጪው የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም በዱባይ…

የብሪክስ ሀገራት 45 ትሪሊየን ዶላር ኢንቨስት ሊደረግ የሚችል ሃብት እንዳላቸው ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪክስ አባል ሀገራት 45 ትሪሊየን ዶላር ኢንቨስት ሊደረግ የሚችል ሃብት እንዳላቸው የሄንሌይ እና ፓርትነርስ የብሪክስ የሃብት ሪፖርት አመላከተ፡፡ ቀደም ሲል ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካና ብራዚል አቅፎ የነበረው ብሪክስ ፥ በአሁኑ…

አቶ ጥላሁን ከበደ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ለሚካሄደው 9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የዝግጅት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። 9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም “የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ከየካቲት 9…

ሸበሌ ዞን የግብርና ዘርፍ ስብራታችንን ለመጠገን የጀመርነው ጉዞ ውጤታማ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሸበሌ ዞን የግብርና ዘርፍ ስብራታችንን ለመጠገን የጀመርነው ጉዞ ውጤታማ ስለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ቤርዓኖ ወረዳ በአርሶ አደሮች፣ ባለሀብቶች እና…

ሰባስቲያን ሃለር – ካንሰርን ድል ከመንሳት እስከ አፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮትዲቯሩ አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር ከካንሰር ሕመም በማገገም ሀገሩ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን እንድትሆን የአንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል፡፡ የቀድሞው የአያክስ እና ዌስትሃም አጥቂ ሰባስቲያን ሃለር የጀርመኑን ክለብ ቦርሺያ ዶርትሙንድ ከተቀላቀለ በኋላ…

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሰላምና ልማት ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ዛሬ ማለዳ ባሕር ዳር ከተማ ገብቷል፡፡ እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይም…

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 04፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የመጀመሪያውን ምዕራፍ አጠናቆ የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስታወቀ። ኮሚሽኑ በሰጠው መግለጫ፤ እስካሁን በተሰራው ስራ የተሳታፊዎች ልየታን ጨምሮ ለምክክሩ ሂደት ጠቃሚ የሆኑ በርካታ ስራዎች…

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል

አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ፒያሳ አካባቢ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከነገ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳስታወቁት÷የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከነገ ጀምሮ በሚወጣው…

በሚቀጥሉት 10 ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – ኢንስቲትዩቱ

አዲስ አበባ፣የካቲት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሚቀጥሉት 10 ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ከዕለት ወደ ዕለት እንደሚጠናከሩ የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ በዚህ መሰረትም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ የመካከለኛው ኢትዮጵያና የምሥራቅ…