ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከኢንፔሪያልና ሪቬራ ሆቴል ግዢ ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ተባሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከኢንፔሪያል እና ሪቬራ ሆቴል ግዢ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው።
የጥፋተኝነት ፍርዱን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።…