Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ስታዲየም የሳር ንጣፍ ሥራ በቅርቡ ለማስጀመር እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መመዘኛ መስፈርትን ተከትሎ እድሳት እየተደረገለት ያለው የአዲስ አበባ ስታዲየም የሳር ንጣፍ ሥራ ለማስጀመር እየተሰራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ። ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ…

በፋይናንስ ተቋማት ያለው የቁጠባ ገንዘብ መጠን ከ2 ትሪሊየን ብር በላይ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያለው የቁጠባ ገንዘብ መጠን ከ2 ትሪሊየን ብር በላይ ማለፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ ሰለሞን ደስታ÷ የሕብረተሰቡ የቁጠባ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻልና ለውጥ…

አቶ አወል አርባ በገቢ ረሱ ቦሎይታ ቀበሌ የጤፍ ማሳን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በገቢ ረሱ ቦሎይታ ቀበሌ በ200 ሔክታር ላይ እየለማ የሚገኘውን የጤፍ ማሣ ጎብኝተዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የጀመርነውን…

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ዛሬ ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡ ውጤቱ÷ ዛሬ ከምሽቱ 3 ሠዓት ጀምሮ ይፋ መደረጉን ነው አገልግሎቱ ያስታወቀው፡፡ ተፈታኞችም…

ተቀዛቅዞ የቆየው የቱሪዝም ዘርፍ እያገገመ መምጣቱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በመጀመሪያዎቹ ሰባት  ወራት የዓለም ቱሪዝምን በመሳብ 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን የዓለም አቀፉ ቱሪዝም ተቋም አስታወቀ፡፡ ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2019 አንጻር 28 በመቶ የቱሪዝም ፍሰት ዕድገት በማስመዝገብ…

በመተከል ዞን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የተከናወነው ሥራ ተገመገመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር የተከናወነው ሥራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡ በክልሉ የተገኘውን ሰላም ለማፅናት ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ፈጠራና የሕዝብ ግንኙነት ሥራ መሠራት…

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የብሔራዊ ቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ኃይሌ ረዳቶቻቸውን አሳውቀዋል።…

የፀጥታ መዋቅሩ ከሠራዊቱ ጋር በመቀናጀት ሠላም የማረጋገጥ ሥራ እያከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐይቅ ከተማ የፀጥታ መዋቅር ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ የሚሠጠውን ግዳጅ መፈፀም በሚያስችለው ቁመና ላይ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል ሲሉ ብርጋዲየር ጄኔራል ዘውዱ ሠጥአርጌ ገለጹ፡፡ በቀጣናው ሕገ-ወጥ ቡድኖችን ለማፅዳት ሠራዊቱ በሚያከናውነው…

ለሁሉም ምቹ የሆነች ሀገርን ለመፍጠር የሚያስችል የሪፎርም ሥራ እየተሠራ መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁሉም ምቹ የሆነች ሀገርን ለመፍጠር የሚያስችል የሪፎርም ሥራ እየተሠራ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። የሪፎርም መሰረታውያንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሚና በሚል ርዕስ በአፍሪካ አመራር ልኅቀት…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተጋላጭ ሴቶችና ሕፃናት ማቆያ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተጋላጭ ሴቶችና ሕፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ ተመረቀ፡፡ በክልሉ ሆሞሻ ወረዳ የተገነባው ማዕከል የሴቶችን ደኅንነት የመጠበቅ እና ፍትሕ እንዲያገኙ የማሥቻል ብሎም ሴቶች ላይ ከሚደርስ ተፅዕኖ የመከላከል ሥራዎች…