Fana: At a Speed of Life!

ዶላር አባዛለሁ በሚል ከአንዲት ግለሰብ 175 ሺህ ዶላር የወሰደው ተከሳሽ በ11 ዓመት እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶላር አባዛልሻለሁ በሚል አንዲት ግለሰብን በማታለል 175 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የወሰደው ግለሰብ በ11 ዓመት እስራት ተቀጣ፡፡ ወንጀሉ የተፈፀመው ከሕዳር እስከ የካቲት ወር 2014 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ በተለያዩ ቀናት በየካ ክፍለ ከተማ…

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ የሦስትዮሽ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሠሪ፣ ሠራተኛ እና መንግሥት አማካሪ ቦርድ የሦስትዮሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ ላይ ÷ የሥራና ክኅሎት ሚንስቴር፣ ጤና ሚንስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የሁለቱ አሠሪዎች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን አማካሪ ቦርድ አባላት ተሳትፈዋል፡፡…

ትምህርት ሚኒስቴር ብቁ መምኅራንን ለማፍራት እየሠራ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ምዘና ሥርዓቱን ለማሻሻል እና ብቁ መምኅራንን ለማፍራት እየሠራ መሆኑን ትምሕርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በጅግጅጋ ከተማ ለሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 36ኛው የመምኅራን ማኅበር ጉባዔ ተጠናቅቋል። የትምሕርት ሚንስትሩ ብርሃኑ ነጋ…

በሲዳማ ክልል የበጋ መስኖ ልማት ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የ2016 ዓ.ም የበጋ መስኖ ልማት ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል፡፡ በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የሥራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡…

የኢትዮ-ጅቡቲ ትራንስፖርት ፍሰት ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ ትራንስፖርት ፍሰት ሠላማዊና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአፋር ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ሁሴን ቦልኮ እንደገለጹት÷ የሀገሪቱን ቁልፍ…

ስለ ሀሞት ጠጠር አጋላጭ ምክንያቶች ምን ያህል ያውቃሉ?

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐሞት ከረጢት/ፊኛ ጠጠር በተለምዶም የሐሞት ጠጠር የሚባለው የሐሞት ፊኛ ውስጥ ጠጠር ሲከማች ነው። ይህ ጠጠር ለምን እና እንዴት እንደሚፈጠር ሳይንሳዊ ድምዳሜ ላይ መድረስ ባይቻልም የተለያዩ መላምቶችን ግን መጥቀስ ተችሏል። እነዚህም…

አቶ አብነት ገ/መስቀልን ጨምሮ በ5 ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ አቶ አብነትገ/መስቀል እና 3 የመሬት አስተዳደር ሰራተኞች የተካተቱበት ባጠቃላይ በአምስት ግለሰቦች ላይ የሙስና ወንጀል ክስ መስርቷል። አቶ አብነት ገ/መስቀል በቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 2…

የቀድሞው የስፔን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት የሶስት አመት ዕግድ ተላለፈባቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በቀድሞው የስፔን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቢያሌስ ላይ ዕገዳ አስተላለፈ። ፊፋ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ከማንኛውም ስፖርታዊ ጉዳዮች ለሶስት አመታት እንዲታገዱ ነው ውሳኔ ያሳለፈው።…

ነፃ የቴአትር ማስታወቂያ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 19 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነፃ የቴአትር ማስታወቂያ ለቴአትር ባለሙያዎች ሰጠ። ነፃ የየቴአት ማስታወቂያው ለአንድ አመት የሚቆይ ሲሆን የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ማስታወቂያ በነፃ ለሁሉም የቴአትር አዘጋጆች ነው የተሰጠው። የፊርማ…

የአዕምሮ ህሙማንን በሰንሰለት ማሰር ሊታገድ እንደሚገባ ሂዩማን ራይትስ ዎች አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች የአዕምሮ ህሙማንን በሰንሰለት ማሰር ሊታገድ እንደሚገባ አሳስቧል። ድርጅቱ የአዕምሮ ህሙማንን አያያዝ አስመልክቶ በጋና ሁለት ማዕከላት ላይ ባደረገው ጥናት፥ ጋና በፈረንጆቹ 2017…