Fana: At a Speed of Life!

በሸገር ከተማ ቡራዩ ክ/ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ አደጋ 13 ሱቆች ወደሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ጸራ ጽዮን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በንግድ ሱቆች ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በእሳት አደጋው የተለያየ የንግድ ስራ የሚከናወንባቸው 13 ሱቆች መቃጠላቸውን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት…

በአዲስ አበባ ከደረጃ በታች የሆኑ 12 ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደረጃ በታች በሆኑ 12 ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ባለስልጣኑ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፥ በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት መሰረት የግል ት/ቤቶችን…

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን እንስሳት ልማትና ልኅቀት ማዕከል መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንስሳት ልማትና ልኅቀት ማዕከል መርቀው ከፈቱ፡፡ ማዕከሉ በ140 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን፥ በዘርፉ…

በድሬዳዋ ከተማ ዘንድሮ 2 ሚሊየን ችግኝ ይተከላል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የክረምት ወራት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 2 ሚሊየን ችግኝ እንደሚተከል የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ብሩክ ፈለቀ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ኤልሲሲ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግብጽ ካይሮ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታሕ ኤልሲሲ ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል "በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትብብር በሰፈነበት መንፈስ ውይይቶች አካሂደናል" ብለዋል።

በሶማሌ ክልል በአንድ ጀንበር 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በአንድ ጀንበር 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ኃላፊ አብዱልቃድር ረሺድ እንደገለጹት÷ 1 ሚሊየኑ በጅግጅጋ ከተማ ይተከላል፡፡ ቀሪው 4 ሚሊየን በክልሉ በተለያዩ ዞኖች…

አቶ ደመቀ የኢትዮ-ኬንያ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮ-ኬንያ ሁለንተናዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እየተሠራ መሆኑን ገለጹ። አቶ ደመቀ ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው 43ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አሥፈጻሚ ምክር…

ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የኢጋድ ጥረት የቀጣናው ሀገራት በልማት እንዲዋሃዱ ነው አሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ጥረት በቀጣናው መረጋጋት እንዲሰፍንና ሀገራቱ በልማት ሥራዎች እንዲዋሃዱ መሆኑን ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)ገለጹ፡፡ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በለንደን “ቻትሃም”…

በሐረሪ ክልል ሕዝቡ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ሕዝቡ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በንቃት እንዲሳተፍ የክልሉ ግብርና ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ሻሚ አብዲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በክልል ደረጃ 2 ነጥብ…

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ  አመራሮች በሰላምና ደኅንነት ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በሰላምና ደኅንነት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ÷ አዲስ አበባ…