Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከኢትዮጵያም ሆነ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለፀች፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በጎንግ ዌቢን(ፕ/ር) ከተመራው የቻይና ብሄራዊ የአስተዳደር አካዳሚ የልዑካን ቡድን ጋር የሁለቱን ሀገራት…

ህብረተሰቡ ግላዊ መረጃዎችን ከአጭበርባሪዎች እንዴት መጠበቅ አለበት?

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁሉም ሰው የኢንተርኔት ዓለም እውነታዎችን መረዳት እና ማወቅ አለበት፡፡ በኦንላይ የሚደረጉ ግብይቶች፣ የመረጃ ልውውጦች እና የምናጋራቸው መረጃዎች እንዴት በእውነተኛ ህይወት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ማወቅ እና መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡…

በሰባቱ አመቱ ጦርነት የተጻፉ ደብዳቤዎች ከ265 ዓመታት በኋላ ተነበቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደ አሁኑ ማሕበራዊ ሚዲያ ተደራሽ ባልሆበነበት ዘመን ሰዎች ሰላምታቸውን፣ ፍቅራቸውን፣ ናፍቆታቸውንና ፍላጎታቸውን በወረቀት አስፍረው ለልባቸው ሰው እንዲደርስ በመልክተኛ ይልካሉ፡፡ መልዕክተኛው በቶሎ ካደረሰው እሰየው ብለው ምላሽን ይጠባበቃሉ ፤…

የቡድን 7 አባል ሀገራት በጋዛ እና በዩክሬን ጉዳይ ቶኪዮ ላይ ሊመክሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡድን 7 አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቶኪዮ ላይ ተገናኝተው በጋዛ እና በዩክሬን ጉዳይ ሊመክሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ዛሬ እና ነገ የሚካሄደውን ስብሰባ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮኮ ካሚካዋ ይመሩታል ተብሏል፡፡ ካሚካዋ አስቀድመው…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤሌክትሮኒክ ግብይት ለሚገዙ እቃዎች የካርጎ ማዕከል ወደ ሥራ ሊያስገባ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤሌክትሮኒክ የግብይት ሥርዓት ለሚገዙ እቃዎች (ኢ-ኮሜርስ) የሚውል የካርጎ ማዕከል በቅርቡ ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፥የካርጎ አገልግሎቱን…

የአርቲስት አሊ ቢራ ህይወት ያለፈበት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ-ስርዓት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት አሊ ቢራ ህይወት ያለፈበት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ-ስርዓት በተለያዩ ዝግጅቶች በድሬዳዋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡ በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መግቢያ አካባቢ በተዘጋጀ የአርቲስቱ የቢልቦርድ ምርቃት የጀመረው…

132 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተላኩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 132 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በሁለት ዙር ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ገለጹ፡፡ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳስታወቁት፥ ስደት በዜጎች ላይ የሚፈጥረውን…

አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ‘የኛ ምርት’ የተሰኘ ኤግዚቢሽንና ባዛር በመጪው ታህሳስ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣2016፣ (ኤፍ ቢ ሲ) አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ኤግዚቢሽንና ባዛር ''ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት'' በሚል መሪ ሃሳብ ከታህሳስ 3 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል። አምራች…

ሀገራዊ የፋይናንስ አቅም የዋጋ ንረትን ሊያረጋጋ በሚችልና የስራ እድልን በሚፈጥሩ ዘርፎች ላይ ማዋል እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ውስጥ ያለውን ውስን ፋይናንስና የኢንቨስትመንት አቅም የዋጋ ንረትን ሊያረጋጋ በሚችል፣ የስራ እድልን በሚፈጥሩና የውጭ ምንዛሬን ሊያስገኙ በሚችሉ ዘርፎች ላይ ማዋል እንደሚገባ ተመላከተ። ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው…

ሊቢያ 600 ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ግብፃውያን ወደሀገራቸው ልትመልስ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊቢያ በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ 600 ሰነድ አልባ የግብፅ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ልትመልስ መሆኗ ተገልጿል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሊቢያ የሚገኙ ፍልሰተኞችን ወደ አሀራቸው የመመለስ ሃላፊነት የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች…