Fana: At a Speed of Life!

ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የሚሰጥ ከ16 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በድርቅ እና በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ከ16 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ የብሪታኒያ መንግስት አስታወቀ፡፡ የብሪታኒያ የልማት ሚኒስቴር አንደሪው ሚሸል እንደገለፁት ፥ ድጋፉ ትግራይን ጨምሮ በድርቅ እና በግጭት ሳቢያ ለተጎዱ…

አቶ ሞገስ ባልቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበርያ ፅ/ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ሞገስ ባልቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ማስተባበርያ ፅ/ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡ ለአቶ ሞገስ ባልቻ ሹመት የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መሆናቸውን ከከንቲባ…

የአዲስ-አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ለተሽከርካሪ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ዛሬ ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጉን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታውቋል፡፡   ኢንተርፕራይዙ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ዘሃራ መሃመድ…

በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረትለማጠናከር የስንዴ እርሻ ልማት ትልቅ ሚና አለው – አቶ አወል

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራር በዱብቲ ወረዳ የስንዴ እርሻ ልማትን ጎብኝቷል።   አቶ አወል አርባ በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ በክልሉ የስንዴ ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የእርሻ…

ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻችን የዓለም እንዲሆኑ አንድ መሆንና ሰላም ማስፈን ብቻ ነው የሚያስፈልገን – ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) "ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻችን ይበልጥ እየጎለበቱ የዓለም እንዲሆኑ አንድ መሆንና ሰላም ማስፈን ብቻ ነው የሚያስፈልገን" ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ተናገሩ። ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል ባስተላለፉት…

የጥምቀት በዓል በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በሠላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ። በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን የፀጥታና ደኅንነት አባላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የበዓሉ…

የሶማሌ ክልል የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀም እየገመገመ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል የ2015 የስድስት ወራት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሮች የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሔደ ነው፡፡ በግምገማው ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፣…

ጥምቀትን በአብሮነት በማክበራችን ተደስተናል – የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓመታት ርቆን የቆየው ሰላም ተመልሶ ጥምቀትን በአብሮነት በማክበራችን ተደስተናል ሲሉ የአክሱም ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። የጥምቀት በዓል በታሪካዊቷ አክሱም ከተማና ሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ተከብሯል። አስተያየት…

በሦስት የእሳት አደጋዎች 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ እና አካባቢዋ በተከሰቱ ሦስት የእሳት አደጋዎች 6 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በሦስቱም አደጋዎች በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱ እና ከ900…

በጃንሜዳ በጥምቀት በዓል ላይ ስርቆት ፈጽመዋል የተባሉ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የከተራ እና ጥምቀት በዓል ላይ የስርቆት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የተሰረቁ 20 ሞባይል ስልኮችም በኤግዚቢትነት መያዛቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ…