Fana: At a Speed of Life!

የመረጃ መንታፊዎችን ለመከላከል የሳይበር ደኅንነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀረፃ ላይ በተቋማት መካከል ትብብር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁዋዌ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን የሦስት ቀናት የሳይበር ደኅንነት ሥልጠና መሥጠቱን አስታወቀ። ሁዋዌ ሲሰጥ የቆየውን የሳይበር ደኅንነት ሥልጠና የመሩት ከፍተኛ የሳይበር ደኅንነት ባለሙያዎቹ መሆናቸውም ነው የተጠቆመው።…

አቶ  ሙስጠፌ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር  አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጀግኖች…

ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የመጀመሪያው የበይነመረብ አስተዳደር ጉባዔ የፊታችን ሐምሌ 28 እንደሚካሄድ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የመጀመሪያው የበይነመረብ አስተዳደር ጉባዔ ሐምሌ 28 ቀን 2014 እንደሚካሄድ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሐምሌ 28 ቀን 2014 በአዲስ አበባ የሚካሄደውን ጉባዔውን አስመልክተው…

በአትሌቲክሱ የተገኘው ድል የኢትዮጵያውያንን አንድነት የበለጠ ያጠናከረ ታሪካዊ ድል ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በአትሌቲክሱ የተገኘው ድል የኢትዮጵያውያንን አንድነት የበለጠ ያጠናከረ ታሪካዊ ድል ነው ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና…

የአማራ ክልል ምክር ቤት የተነሱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መብቶችና ጥቅሞችን በተመለከተ የተዘጋጀን አዋጅ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አራተኛ ቀኑን የያዘው የአማራ ክልል ምክር ቤት በተለያዩ አዋጆች ላይ እየመከረ ነው፡፡ የክልሉ ምክር ቤቱ ከሃላፊነት የተነሱ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላት፣ ዳኞች እና ዓቃቢያነ ህግ መብቶች እና ጥቅሞች በተመለከተ ተሻሽሎ…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዘንድሮ 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር አተረፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ማትረፉን አስታወቀ። ባንኩ የ2014 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት እያካሄደ ነው። የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ…

በደቡብ ክልል በአንድ ጀንበር 100 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በአንድ ጀንበር 100 ሚሊየን ችግኝ መትከል የሚያስችል መርሐ ግብር በስልጤ ዞን ምስራቅ ስልጢ ወረዳ ተጀምሯል። የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና…

የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያ የ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪክ ልማት ፈንድ ዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮጵያ የ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታውቋል፡፡ ድጋፉ በኢትዮጵያ በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም እና በምርምር እና ፖሊሲ ትንተና ላይ ያለውን አቅም…

እስራዔል በሥራ ዕድል ፈጠራ ያላትን ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ለማካፈል ቁርጠኛ መሆኗን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከእስራዔል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ውይይቱን አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ እስራዔል በርካታ…

ኢትዮጵያ እና ሕንድ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሕንድ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ባይሳ በዳዳ÷ በደቡባዊ ሕንድ ከሚገኙ…