Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት የአፍሪካ ቢሮ በአዲስ አበባ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት የአፍሪካ ቢሮ በኢትዮጵያ መከፈቱ በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶች ላይ ያላትን የነቃ ተሳትፎ የሚያሳይ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት…

የተባበሩት መንግስታት ኢትዮጵያ በቀጣናው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የሰላም ግንባታ እና ፖለቲካ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሐፊ ሮዝማሪ ዲካርሎ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸው ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሒደት በጥሩ ሁኔታ…

ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ የ5ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ፈጣን የሆነውን የ5ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት በጅማ ከተማ በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በዚህ ወቅት÷ ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግና የኢትዮጵያን የልማት…

ቀነኒሳ በቀለ በ2025 የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት 2025 በሚካሄደው የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታውቋል፡፡ በ40 ዓመት ዕድሜ ላይ የሚገኘው አትሌት ቀነኒሳ የለንደን ማራቶን የመጨረሻው ዓለም አቀፋዊ ውድድር ሊሆን እንደሚችል…

የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደምን የንግድ ትብብር የሚያጠናክር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ፣ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን እና አሴት ግሪን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደምን የጋራ የንግድ ትብብር የሚያጠናክር የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ምክትል ጠቅላይ…

ቼክ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሚሮስላቭ ኮሼክ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርትን በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ የለውጥ ርምጃዎች…

በጉባዔው ኢትዮጵያ የስንዴ ምርትና የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮዋን ለሌሎች ሀገራት አካፍላለች – አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርትና በአረንጓዴ አሻራ ያስመዘገበችውን ውጤት ለሌሎች ሀገራት በተሞክሮነት ማካፈሏን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴዔታ ተስፋሁን ጎበዛይ…

ዓለም ባንክ ዘመናዊ የትራፊክ ስርዓት ዝርጋታ ስራን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ቪክቶሪያ ኳኳ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸው ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ኳኳ (ዶ/ር)÷ በሰው ተኮር ስራ፣…

አየር መንገዱ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ቀዳሚ ምርጫ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የተካፈሉ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ቀዳሚ ምርጫ በመሆኑ ክብር እንደሚሰማው ገልጿል፡፡ 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ተካሂዶ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡…

ጉባዔው ትላልቅ ሁነቶችን በስኬት የማጠናቀቅ አቅማችን አሳይቷል – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በተቋማት ቅንጅት እና በህዝብ ባለቤትነት እየተመራን ትላልቅ ሁነቶችን በስኬት የማጠናቀቅ አቅማችን አሳይቷል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ። 38ኛው የአፍሪካ ህብረት…