Fana: At a Speed of Life!

በድንገተኛ ፍተሻ 18 ኩንታል አደንዛዥ ዕጽ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ ፖሊስ በሻሸመኔ መግቢያ በኩል ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 18 ኩንታል አደንዛዥ ዕጽ መያዙን አስታወቀ፡፡ አደንዛዥ ዕጹ በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ተጭኖ ሲንቀሳቀስ ከሁለት ግለሰቦች ጋር እጅ ከፍንጅ…

 የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባቡር ትራንስፖርቱን አቅም ማሳደግ የሚያስችል የሶስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ይፋ መደረጉን የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ(ኢ/ር) ገለፁ፡፡ ዋና ስራ አስፈፃሚው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው…

የአገው ፈረሰኞችን በዓል በድምቀት ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጥር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚከበረው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ምስረታ በዓል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል፡፡ የመምሪያው ሃላፊ አቶ ለይኩን ሲሳይ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የአገው…

በኦሮሚያ ክልል 94 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 6 ወራት 94 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡ የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ረመዳን ዋሪዮ ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት÷በክልሉ በ2017 በጀት ዓመት 200 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ…

884 ቀበሌዎች ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ነፃ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 884 ቀበሌዎች ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ነፃ መሆናቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በአጠቃላይ ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ነፃ የወጡ ቀበሌዎችን ሽፋን 47 ነጥብ 86 በመቶ መሆኑንም…

ፕሬዚዳንት ፑቲን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆናቸውን ክሬምሊን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር የስልክ ውይይት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ክሬምሊን አስታወቀ፡፡ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ ከትራምፕ ጋር ለሚደረገው ውይይት የዋሽንግተንን ምላሽ…

359 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሊባኖስ እና በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 359 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡ በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ እና ለአደጋ የተጋለጡ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ…

ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ ክትትል ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እና በጀት በጥራት እንዲጠናቀቁ ክትትል ማድረግ እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡ ቋሚ ኮሚቴው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴርን…

በኦሮሚያ ክልል የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል የቱሪስት መዳረሻዎችን የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ። በቢሮው የቱሪዝም ልማትና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ፋንታሁን ታደሰ፤ በክልሉ የቱሪስት መዳረሻዎች ልማት…

ቪፓር የተሰኘ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ መሠማራት እንደሚፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕንዱ ቪፓር የተሰኘ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ መሠማራት እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴዔታ ሀሰን መሀመድ ከኩባንያው ተወካዮች ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡ በዚሁ…