Fana: At a Speed of Life!

ሠራዊቱ ከግዳጁ ጎን ለጎን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን አቅም የመገንባት ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ሠራዊት የቀጣናውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ እየተወጣ ካለው ግዳጅ ጎን ለጎን በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችን አቅም የመገንባት ስራን አጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ። የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ የጊቤ ማሰልጠኛ ለአራት ወራት በሁለት ዙር…

እስራኤል በሌባኖስ በጀመረቸው ዘመቻ ከ440 በላይ የሂዝቦላህ ታጣቂዎችን መግደሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ባለፉት ሦስት ሣምንታት በደቡባዊ ሊባኖስ ባደረገችው ዘመቻ ከ440 በላይ የሂዝበላህ ተዋጊዎችን መግደሏን የሀገሪቱ ጦር አስታወቀ፡፡ የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዲየር ጄኔራል ዳንኤል ሃጋሪ እንደገለፁት ÷ በአየር እና በመሬት ላይ…

የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቋል-የፌደራል ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ የተከበረው የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የፌደራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከኦሮሚያ ፖሊስ፣ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት አካላት፣ ከቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች፣ ከበዓሉ…

በአማራ ክልል ከነገ ጀምሮ የፖሊዮ ክትባት ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ከመስከረም 27 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም በዘመቻ እንደሚሰጥ የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ እንዳስታወቁት÷ ክትባቱ የሚሰጠው…

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተደድር እንዳሻው ጣሰው በ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት አበርክተዋል፡፡ ሽልማቱ የተበረከተው "የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራት" በሚል መሪ ሀሳብ በማረቆ ልዩ…

በጋምቤላ ክልል ሁለተኛው ምዕራፍ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሁለተኛ ምዕራፍ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ የ5 ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል። የመጀመሪያው ምዕራፍ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ላለፉት አምስት ዓመታት ሲተገበር ቆይቷል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ…

የሆረ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሆረ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን አባ ገዳ ጎበና ኦላ አስታውቀዋል። አባ ገዳ ጎበና ኦላ በሰጡት መግለጫ፥ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የእርቅና ወንድማማችነት በዓል የሆነው ሆረ አርሰዲ…

“የሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓላት በስኬት መጠናቀቃቸዉ የኦሮሞን ህዝብ ታላቅነት የሚያረጋግጥ ነው”- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017(ኤፍ ቢ ሲ)"የሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ አርሰዴ የኢሬቻ በዓላት በስኬት መጠናቀቃቸዉ የኦሮሞን ህዝብ ታላቅነት ያረጋገጡ ናቸው"ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ፡፡ ርእሰ መስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷የሆረ ፊንፊኔ እና የሆረ…

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ መሠረታዊ ወታደሮችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብላቴ የሚገኘው የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች በዛሬው እለት አስመርቋል። በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አለምሸት…

በክልሉ በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሽልማት መርሃ ግብር በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። በሽልማት አሰጣጥ መርሃ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን እና…