ስፓርት
ነገሌ አርሲ መቻልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገሌ አርሲ መቻልን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የነገሌ አርሲን የማሸነፊያ ግቦች ዳዊት ተፈራና አለኝታ ማርቆስ አስቆጥረዋል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ከ9 ሰዓት ጀምሮ ሸገር ከተማና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube…
Read More...
ማንቼስተር ሲቲ ከቼልሲ – ተጠባቂው ጨዋታ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ ምሽት 2 ሰዓት 30 ላይ ቼልሲን ያስተናግዳል።
በሊጉ ከተከታታይ ስድስት ጨዋታዎች ድል በኋላ ከሰንደርላንድ ጋር አቻ የተለያየው ማንቼስተር ሲቲ ከመሪው አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ይፋለማል፡፡
አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካን ያሰናበተው…
ሴኔጋል ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ሱዳንን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በተካሄደው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሴኔጋል ፓፔ ጉዬ (ሁለት) እና ምባዬ ባስቆጠሯቸው ሶስት ግቦች ሱዳንን አሸንፋለች።
ሱዳን ከሽንፈት ያልታደጋትን ብቸኛ ግብ አሚር አብደላህ ከመረብ…
ወልቭስ ዌስትሃም ዩናይትድን በማሸነፍ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወልቭስ ዌስትሃም ዩናይትድን 3 ለ 0 በማሸነፍ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሜዳው ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ወልቭስ አሪያስ፣ ዋንግ ሂ-ቻን (በፍጹም ቅጣት ምት) እና ማኔ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ባለፈው…
አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶንቪላ ኖቲንግሃም ፎረስትን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ከ30 በተረደገው ጨዋታ ኦሌ ዋትኪንስ እና ጆን ማክ ጊን (ሁለት) ለአስቶን ቪላ ግቦቹን ሲያስቆጥሩ ሞርጋን ጊብስ ዋይት የኖቲንግሃም ፎረስትን ብቸኛ ግብ ከመረብ አገናኝቷል።
ውጤቱን ተክትሎም…
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ወላይታ ድቻ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያተይተዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቴዎድሮስ ሀይለማሪያም ለወላይታ ድቻ እንዲሁም አቤል ያለው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡…
በአፍሪካ ዋንጫ ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ይደረጋሉ፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ላይ ሴኔጋል ከሱዳን ጋር ይገናኛሉ።
በምድብ ጨዋታዎች ሴኔጋል ሁለቱን በማሸነፍ እና በአንድ ጨዋታ አቻ በመለያየት በሰባት ነጥብ ከምድቧ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች ሲሆን፤ ሱዳን…