Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በኢኮኖሚ መስክ ጠንካራና ልዑላዊነቷን ያስከበረች እንድትሆን የያዘችውን ጥረት ማጠናከር ይገባል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አፍሪካ ከፖለቲካ ነፃነት ባሻገር በኢኮኖሚም መስክ ጠንካራና ልዑላዊነቷን ያስከበረች እንድትሆን የያዘችውን ጥረት ማጠናከር ይገባናል አሉ በአኅጉሪቱ በኢኮኖሚ ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ባለድርሻ አካላት። የዘርፉ ተዋንያን በናይጄሪያ አቡጃ ከተማ በተጀመረው…

ከመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ጋር የተደረገው ምክክር የጋራ ትርክትን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከመንግስት ጋር ተቀራርበው መምከራቸው የጋራ ትርክትን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል አሉ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ምሁራን። ውይይቱ ሀገራዊ የልማት አጀንዳዎችን የመፈጸም አቅም በማስረጃ በማስደገፍ ለማቅረብ…

በክልሉ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የጤና ተቋማት ግንባታ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የጤና ተቋማት ግንባታና ማስፋፊያ እየተከናወነ ይገኛል። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በክልሉ የጤና ተቋማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥና አገልግሎቱን…

የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየተሰራ ነው – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን እየተሰራ ነው አሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና አሰጣጥ ሂደቱን…

በደብረ ብርሃን ከተማ አንዲት እናት አራት ልጆችን በሰላም ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው ሃኪም ግዛው ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም ተገላግላለች። በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሀኪም ዶ/ር አዲሱ ግርማ የ38 ዓመቷ እናት የባሶና ወራና ወረዳ መምጣቷን…

ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ቁርጠኝነት የሚታይበት የመገጭ መስኖ ግድብ…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ለፍጻሜ የማብቃት ቁርጠኝነትን በሚያሳይ መልኩ እየተከናወነ ነው፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት ያደረጉ የሕዝብ እና የግል ሚዲያዎች እንዲሁም የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች…

በወላይታ ሶዶ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ በዛሬው ዕለት በደረሰው የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የሶዶ ከተማ ፖሊስ ዋና አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት÷ በወላይታ ሶዶ ከተማ የፍሳሽ ማስወገጃ ተሽከርካሪ…

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሁሉም ዜጎች በእኩል የሚስተናገዱበት አካታች ሥርዓት ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሁሉም ዜጎች በእኩል የሚስተናገዱበት አካታች ሥርዓት ነው አሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሀይ ጳውሎስ። የ10ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር…

የአካባቢውን ታሪክና የተፈጥሮ ጸጋ ያጣመረው ሀላላ ኬላ ሪዞርት…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የሀላላ ኬላ ሪዞርትን ጎብኝተዋል። ባለሙያዎቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ከተወያዩ በኋላ ነው ዳውሮ ዞን የሚገኘውን ሀላላ ኬላ የጎበኙት፡፡ የገበታ ለሀገር ኮይሻ…

ቱሪዝምን ከግብርና ያስተሳሰረው ቤኑና መንደር…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከመንግስት እና ከግል ሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ ባለሙያዎቸ በበሰቃ ሃይቅ ዳርቻ የተገነባውን የቤኑና መንደር ጎብኝተዋል። የቤኑና መንደር እጅግ ዘመናዊ መኝታ ክፍሎች፣ አዳራሽ፣ ሲኒማ ቤት የመዝናኛ ሥፍራዎች፣ ስፓ እንዲሁም የፍራፍሬ ልማትና…