Fana: At a Speed of Life!

በእውቀትና ሥነምግባር የታነጸ ትውልድ በመፍጠር ሂደት የመምህራን ሚና የላቀ ነው – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል በእውቀትና ሥነምግባር የታነጸ ትውልድ በመፍጠር ሂደት የመምህራን ሚና የላቀ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ። “ትውልድ በመምህር ይቀረጻል፤ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ሀሳብ ከክልሉ መምህራን…

ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሀብት ዘመኑን በዋጀ መልኩ ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በውሃ ሀብትና በኢነርጂ ዘርፍ ያላትን ሀብት ዘመኑን በዋጀ መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል ስራ እያከናወነች መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ። ሚኒስቴሩ በውሃ እና ኢነርጂ ረቂቅ የፖሊሲ…

ሊቨርፑል ድሉን ከደጋፊዎቹ ጋር እያከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2024/25 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ድሉን ከደጋፊዎቹ ጋር እያከበረ ይገኛል። የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በአንፊልድ ጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር ከደጋፊዎቹ ጋር 20ኛ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ድሉን…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሲዳማነት የተጠቃ መሬትን የማከም ሥራ እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሲዳማነት የተጠቃውን መሬት በማከም የአፈር ለምነትን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል። የቢሮው ምክትልና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አንደኛ ሽናሌ÷ በክልሉ ከሚታረሰው ከ1 ነጥብ 3…

ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት የመላው አማራ ጨዋታዎች ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደሴ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 9ኛው መላው አማራ ጨዋታዎች ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። ከግንቦት 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ “ስፖርት ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ በቆየው ውድድር÷ በ19 የስፖርት አይነቶች ከ18 ዞኖችና…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለስራ ጉብኝት ፈረንሳይ ፓሪስ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ጋር በመሆን ለስራ ጉብኝት ዛሬ ፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓሪስ ሲደርሱ በብሔራዊው የጦር ኃይሎች ሙዚየም የአቀባበል…

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ1 ሚሊየን በላይ ህፃናት የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ተከተቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከግንቦት 6 ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የተቀናጀ የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ እስካሁን 1 ሚሊየን 31 ሺህ 306 ህፃናት መከተባቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ ሳሙኤል ዳርጌ እንደተናገሩት፤ ክትባቱ…

የቀይ ባሕር አካባቢን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ የቀጣናው ሀገራት ትብብር ወሳኝ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀይ ባሕር አካባቢን የጂኦ-ፖለቲካ ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ የቀጣናው ሀገራት ትብብር ወሳኝ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ ተናገሩ። 3ኛው የቀይ ባሕር ቀጣናዊ ጂኦ-ፖለቲካ ፎረም "የቀይ ባህር እና የኤደን…

መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ ትኩረት በመስጠት አዳዲስ ታሪካዊ ስፍራዎችን አልምቷል – ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ቅርሶች እና አዳዲስ ታሪካዊ ስፍራዎች ማልማቱን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለጹ። ሁለተኛው የቅርስ ምርምር ጉባኤ እና የአውስትሮሎፒከስ አፋራንሲስ (የሉሲ ወይም ድንቅነሽ) አጽም የተገኘበት 50ኛ…

ለ11 ሚሊየን ህፃናት የኩፍኝ ክትባት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአንድ ሳምንት ውስጥ ለ11 ሚሊየን ህፃናት የኩፍኝ ክትባት መሰጠቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀገር አቀፍ ደረጃ ኩፍኝን ጨምሮ በየጊዜው የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ለመከላከል የሚያስችል የተቀናጀ የክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል። በጤና…