Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አሻድሊ ሀሰን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ አሻድሊ ሀሰን በድጋሚ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በምክር ቤቱ ተሹመዋል። ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ አሻድሊ ሀሰንን በድጋሚ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ጉባዔውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 1ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ አካሂዷል። 6ኛው ሀገራዊ የድጋሚ እና የማሟያ ምርጫ በክልሉ መካሄዱን ተከትሎ ምክር ቤቱ ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ጉባዔ ሐምሌ 21 ቀን 2016…

የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ለጎፋ ዞን 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አምስት ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል። ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት የደቡብ ኢትዮጵያ…

በባህር ዳር የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ሃይል ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አገልግሎቱ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ በከፍተኛ መስመር ላይ ባጋጠመ ጉዳት በተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡ ትናንት ምሽት 1 ጀምሮ ከባህር ዳር ቁ.2 የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ በተዘረጋ 15 ኪሎ ቮልት ኤሌክትሪክ…

ገጠሩን ብቻ ሳይሆን ከተሞችንም አረንጓዴ ያለበስንበት አረንጓዴ ዐሻራ ዓለም አቀፍ መለያችን ሆኗል- ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ገጠሩን ብቻ ሳይሆን ከተሞችንም አረንጓዴ ያለበስንበት አረንጓዴ ዐሻራ ዓለም አቀፍ መለያችን ሆኗል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቢሾፍቱ…

በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ንጋት 11 ሠዓት ከ14 ላይ በንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 ሰፈራ አካባቢ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው፡፡ አደጋው የተከሰተው ሰባት ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ…

የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ብድር አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አስፍጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ ለአራት ዓመት የ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን አጽድቋል፡፡ አይ ኤም ኤፍ ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- የዓለም…

በመዲናዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ መሪነት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ተጎብኝተዋል። የብልጽግና ፓርቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በጋራ ያዘጋጁት ስልጠና ተጠናቅቋል።…

 የአደይ አበባ ስታዲየም በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ይገባል – ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአደይ አበባ ስታዲየም ግንባታ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተከናውኖ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ይገባል ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሯ በአደይ አበባ ስታዲየም በመገኘት የስታዲየሙን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸምና…

የኢትዮጵያ እና ቻይናን ትብብር በይበልጥ ለማጎልበት እንሠራለን – ቻይናውያን ጋዜጠኞች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ቻይና ትብብርና ወዳጅነት እንዲዳብርና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱም በይበልጥ እንዲጎለብት በሙያችን እንሠራለን ሲሉ ቻይናውያን ጋዜጠኞች ገለጹ፡፡ ከቻይና 'ፒፕልስ ደይሊ' ጋዜጣ የተውጣጣ የጋዜጠኞች ልዑክ የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን…