Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ሩሲያ ወዳጅነት በፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮጵያና ሩሲያ ወዳጅነት በፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብልጽግና ፓርቲ ጥረት ማድረጉን እንደሚቀጥል የፓርቲው የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለጹ፡፡…

ከንቲባ አዳነች በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፣ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ፣ኤርትራ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያዩ፡፡ በውይይታቸውም ÷በመዲናዋ በዓለም ባንክ የሚደገፉ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ስለሚጠናቀቁበት…

ሀሰተኛ ሊብሬና ታርጋ በማውጣት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉሙሩክ ስርዓት ሳይፈጽሙ ሀሰተኛ የተሽከርካሪ ሊብሬና ታርጋ በማወጣት ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ። የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ወንጀል…

አቶ አሕመድ ሺዴ የአፍሪካ ልማት ባንክ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ በቀጣይ ለሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ጠንካራ ትብብር እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲያደርግ የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ ጠየቁ፡፡ አቶ አሕመድ በአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ዋና ዳይሬክተር ጆናታን ንዛይኮሬራ…

በ45 ሚሊየን ዶላር የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ማሻሻያ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተመረጡ 10 ከተሞች የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት መልሶ ግንባታና አቅም ማሻሻያ ፕሮጀክት ቀርፆ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ፡፡ የፕሮጀክቱ ተግባራዊ መደረግም በዲስትሪቢዩሽን መስመሮች እርጅና ምክንያት…

አቶ እንዳሻው ጣሰው በበጋ ወቅት መደበኛ መስኖ 70 ሺህ ሔክታር መልማቱን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በበጋ ወቅት በመደበኛ መስኖ 450 ሺህ የሚሆኑ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ 70 ሺህ ሔክታር በአትክልትና ፍራፍሬ መልማቱን የክልሉ ም/ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ባለው የክልሉ…

ሀገር አቀፍ የፍትሕ ተቋማት የጋራ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር አቀፍ የፍትሕ ተቋማት የጋራ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፍትሕና የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የክልሎችና…

እስራኤልና ሃማስ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ የ40 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጦርነት ውስጥ የሚገኙት እስራኤል እና ሃማስ በመጪው የረመዳን ወር የተኩሰ አቁም ለማድረግ መቃረባቸውን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተናገሩ፡፡ ባይደን ስለ ወቅታዊው የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት አስመለክተው እንደተናገሩት÷ ሃማስ ከረመዳን…

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከወላይታ ዞን በምክክሩ የሚሳተፉ ተወካዮችን መረጣ ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከወላይታ ዞን በሀገራዊ ምክክሩ የሚሳተፉ የማህብረሰብ ተወካዮችን መረጣ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ኮሚሽኑ በክልሉ 12 ዞኖች ከዚህ በፊት ባሰለጣናቸው ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በተወጣጡ ተባባሪ አካላት ታግዞ…

የህዝቡን ሰላምና ልማት ለማስቀጠል በተሰራ ሥራ ውጤት ተገኝቷል – ሌ/ል ጄ/ል መሠለ መሰረት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝቡን ሰላምና ልማት ለማስቀጠል በተሰራ ሥራ ውጤት ተገኝቷል ሲሉ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሠለ መሰረት ገለጹ፡፡ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሠረት በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በመገኘት ከዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ፀጥታ…