Fana: At a Speed of Life!

በበልግ ወቅት የነበረው የአየር ጠባይ ትንበያ የተከሰተው ድርቅ በዜጎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር አስችሏል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበልግ ወቅት የነበረው የአየር ጠባይ ትንበያ በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተው ድርቅ በዜጎች ላይ ጉዳት ሳያደርስ መቋቋም ማስቻሉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ገለፁ። የበልግ ወቅት የአየር ጠባይ ትንበያ ግምገማና…

በኦሮሚያ ክልል መንግስት የ2015 እቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል መንግስት በቀጣዩ 2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ በውይይት መድረኩ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የካላስተር አስተባባሪዎች…

በደቡብ ክልል ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ክልል ከ11 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቋል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የኢንቨስትመንትና ዳያስፖራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደምሰው ባቾሬ…

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው። የሊጉ ማዕከላዊ ኮሚቴ በመደበኛ ስብሰባው ትናንት በሊጉ ስራ አስፈፃሚ ውይይት ተደርጎባቸው በቀረቡለት የግምገማ ውጤቶችና የውሳኔ ሃሳቦች ላይ ተወያይቶ…

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ የሚመረቱ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት የሕብረቱ ኮሚሽን በጠራው ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ የሚመረቱ የኮቪድ-19 ክትባቶችን በሚመለከት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በጠራው የበይነ መረብ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ተሳትፈዋል። ስብሰባው የአፍሪካ የክትባት ምርት የዓለም አቀፍ የገበያና የሥርጭት…

የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት እና ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እንሰራለን – የፌዴሬሽን ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዴሞክራሲ ባህል እንዲጎለብት እና ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን እንደሚሰራ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ ከሁሉም ክልልና የሁለቱም ከተማ አስተዳደር የፍትህ አካላት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡…

ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው መድሃኒትና የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋሟት ጋር በጋራ በመሆን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው መድሃኒትና የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ…

ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ዛሬ ንጋት ላይ መታየቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢኒስቲቲዩት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፊል የጨረቃ ግርዶሽ ዛሬ ንጋት መታየቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ እስፓሻል ኢኒስቲቲዩት አስታውቋል፡፡ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢኒስቲቲዩት እንዲሁም ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ጋር በመተባበር የጨረቃ ግርዶሽ…

የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ መግባት መቀጠላቸውን ተመድ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው÷በትግራይ እና አፋር ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚሰራጨው…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለተመራጩ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በደስታ መግለጫቸው፥ ከፕሬዚዳንት ሞሀመድ ጋር ለኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጋራ በሆኑ ሁለትዮሽ እና…