Fana: At a Speed of Life!

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን እያገኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን እያገኙ ነው አለ በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት። በኢኒስቲትዩቱ የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ከሰኔ ወር ጀምሮ…

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ለማህበራዊ መስተጋብር፣ ለኢኮኖሚ ፈጠራ እና ለዓለም አቀፍ ተሳትፎ ኃይል ሆኗል – ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ለማህበራዊ መስተጋብር፣ ለኢኮኖሚ ፈጠራ እና ለዓለም አቀፍ ተሳትፎ ኃይል ሆኗል አለ ብልጽግና ፓርቲ። ፓርቲው የአረንጓዴ አሻራን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ በመትከል ማንሰራራት እንደሚቻል አርአያ ሆና…

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ጅግጅጋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በነገው ዕለት በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ጅግጅጋ ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ የውብ ባህል ባለቤት፣…

በመኪና አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ ሲጓዝ የነበረ አይሱዚ መኪና በተለምዶ ሀረጎ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በመገልበጡ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል። የመኪና መገልበጥ አደጋው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ የደረሰ መሆኑ ተገልጿል። የኮምቦልቻ ከተማ…

የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው የኢትዮያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቷል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከብሮድካስት እና ስም ስያሜ መብት የሚያገኙት ክፍፍል ይፋ አድርጓል።…

በአፋር ክልል በአንድ ጀንበር ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል በነገው ዕለት በአንድ ጀንበር ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ አለ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ። ቢሮው ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ እንደገለጸው÷ በነገው ዕለት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን…

በሲዳማ ክልል በአንድ ጀንበር 8 ሚሊየን ችግኝ ይተከላል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በክልሉ በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 8 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል አለ ። በቢሮው የተፈጥሮ ሀብትና አነስተኛ መስኖ ልማት ዳይሬክተር አቶ በረከት አሰፋ ለፋና ዲጂታል…

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በጅማ ዞን በሻሻ ከተማ ያስገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በጅማ ዞን በሻሻ ከተማ ያስገነባውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ቀን መርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል። በምርቃት መርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና…

ባየርን ሙኒክ ሉዊስ ዲያዝን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባየርን ሙኒክ ኮሎምቢያዊውን የመስመር አጥቂ ሉዊስ ዲያዝን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ የጀርመኑ ኃያል ክለብ ባየርን ሙኒክ የ28 ዓመቱን የሊቨርፑል የመስመር አጠቂ ተጫዋች በ65 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ ዋጋ የግሉ አድርጓል። ኮሎምቢያዊው…

ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በሐረር ከተማ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አራተኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ሐምሌ 28 እና 29 ቀን 2017 ዓ.ም በሐረር ከተማ ይካሄዳል። የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የሰላም ጉባኤውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ጉባኤው በሃይማኖት…