Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ሕዝብና ቤት ቆጠራ እየተጓዘች ነው – አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ኢትዮጵያ ወደ ሙሉ የዲጂታል ሕዝብና ቤት ቆጠራ እየተጓዘች ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ 9ኛው የአፍሪካ ስታትስቲክስ ኮሚሽን “አፍሪካዊ ፈጠራን በስታቲስቲክስ ልማት ውስጥ ማስፈን”…

ምክር ቤቱ ነገ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ በመደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ…

እስራኤል በጋዛ የእርዳታ ድርጅቶች ላይ የጣለቸው ክልከላ አሳሳቢ መሆኑን ተመድ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል የእርዳታ ድርጅቶች ለጋዛ ሕዝብ እርዳታ እንዳያቀርቡ የጣለችው ክልከላ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ይበልጥ አስከፊ እንዳደገረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡ የተመድ የሰላም ማስከበር ሃላፊ ጂያን ፒር ላክሮክስ እንዳሉት÷ለጋዛ…

የመዲናችንን የበለጸገ ታሪክ የሚያከብር የቱሪዝም አቅርቦት ለማዳበር የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባን የበለጸገ ታሪክ የሚያከብር የቱሪዝም አቅርቦት ለማዳበር በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ አዲስ አበባ በርካታ ሀገራዊና…

በአማራ ክልል በ80 ወረዳዎች የወባ በሽታ ሥርጭት ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ80 ወረዳዎች የወባ በሽታ ሥርጭት መከሰቱን የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ በተለይም በጎጃም፣ ጎንደር፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ወሎ እና አካባቢዎቻቸው የሚገኙ ከ80 በላይ ወረዳዎች ውስጥ የወባ በሽታ ሥርጭት መስፋፋቱን…

አቶ እንዳሻው ጣሰው ከምሥራቅ ጉራጌ ዞን ወጣቶች ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ መድረክ በቡኢ ከተማ እየተካሄደ ነው። መድረኩ የዞኑን ወጣቶች ለአካባቢያቸው ሰላም፣ ልማት እና እድገት መረጋገጥ…

ጤና ሚኒስቴር 100 ‘ሀርድ ቶፕ’ እና 160 ‘ፒካፕ’ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 572 ሞተርሳይክሎችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጤና ሚኒስቴር 100 ‘ሀርድ ቶፕ’ና 160 ‘ፒካፕ’ ተሽከርካሪዎችን ፣ 572 ሞተር ሳይክሎችን፣ 2 ሺህ 700 ኮምፒውተሮችን ጨምሮ ሞባይል ክሊኒኮችን ለተጠሪ ተቋማቱ፣ ለክልልና ከተማ አሥተዳደር ጤና ቢሮዎች እና ለሆስፒታሎች ድጋፍ አደረገ፡፡…

ኢትዮጵያ እና ጀርመን የ30 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017(ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጀርመን መንግሥት ለተለያዩ ፕሮጄክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል የ30 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የጀርመኑ ኬ ኤ ፍ ደብሊው ልማት ባንክ የፋይናንስ…

ኢትዮጵያ በ19ኛው የኮሜሳ የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እየተሳተፈችበት የያለው የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) 19ኛው የሚኒስትሮች ጉባዔ በቡሩንዲ ቡጁምቡራ እየተካሄድ ነው፡፡ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ሕብርትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ…

አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የጅግጅጋ ነዋሪ ለኮሪደር ልማቱ ላሳየው ትብብር አመሠገኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጅግጅጋ ኮሪደር ልማት ግንባታ የከተማዋ ነዋሪዎች ላሳዩት ቀና ትብብርና ድጋፍ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ምሥጋና አቀረቡ፡፡ ርዕሠ መሥተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ እና የከተማዋ አመራሮች በጅግጅጋ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር…