Fana: At a Speed of Life!

የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ እንደሚያስፈልግ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓን-አፍሪካ የመከላከያ ኃይሎች ትብብርን እውን የሚያደርግ ስትራቴጂ እንደሚያስፈልግ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ። የመጀመሪያው የአፍሪካ መከላከያ ሚኒስትሮች ጉባዔ ከጥቅምት 5 ቀን…

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ገለፁ፡፡ በአፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው…

የሃማስ የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ ያህያ ሲንዋር በእስራኤል ጥቃት ሳይገደል እንዳልቀረ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ የሃማስ ፖለቲካ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው ያህያ ሲንዋር ሳይገደል እንዳልቀረ እስራኤል ገለጸች፡፡ የእስራኤል መከላከያ ሃይል÷ በጋዛ ሶስት የሀማስ ወታደሮችን መግደሉን የገለፀ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ…

የፊስቱላ ሕክምና አገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአራት ክልሎች ብቻ እየተሰጠ የሚገኘውን የፊስቱላ ሕክምና አገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ ለፊስቱላ ህክምና ድጋፍ ከሚያደርገው የሂሊንግ ሃንድስ ኦፍ ጆይ ድርጅት መስራች…

ባንኩ 13 ነጥብ 4 ኩንታል ወርቅ መግዛቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሽረ እንዳስላሴ ቅርንጫፍ በሶስት ወራት ውስጥ ከህጋዊ ወርቅ አዘዋዋሪዎች 13 ነጥብ 4 ኩንታል ወርቅ መግዛቱን አስታወቀ። የቅርንጫፍ ባንኩ ስራ አስኪያጅ አቶ ተኪኤ ግደይ እንደገለፁት÷ ባንኩ ከባህላዊ ወርቅ አምራቾች ግዢ…

ፌዴራል ፖሊስ ወንጀልን በብቃት መከላከል የሚያስችል ጠንካራ ተቋም መገንባቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ወንጀልን በብቃት መከላከል የሚያስችል ጠንካራ ተቋም ገንብቷል ሲሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡ "አፍሪካ በጠንካራ አንድነት፣ ለሁለንተናዊ ፀጥታና ሰላም"…

አሜሪካና ብሪታኒያ የሁቲ አማፂያን ዒላማዎች ላይ ጥቃት ፈፀሙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ እና ብሪታኒያ በየመን ሰነዓ በሚገኙ የሁቲ አማፂያን ዒላማዎች ላይ የተቀናጀ የአየር ጥቃት መፈፀማቸውን አስታወቁ፡፡ የሁቲ አማፂያንን የመረጃ ምንጭ ጠቅሶ አናዶሉ እንደዘገበው÷ አሜሪካ እና ብሪታኒያ በሰሜናዊ እና ደቡብ ሰነዓ በሚገኙ የሁቲ…

ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ወርቅ በህገወጥ መንገድ ይዞ ተገኝቷል የተባለ ግለሰብ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ጥፍጥፍ ወርቅ በህገወጥ መንገድ ይዞ ተገኝቷል የተባለ ግለሰብ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጠ። የፍትህ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት…

በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው በ13 መዝገብ የተከሰሱ ግለሰቦች ከአንድ ዓመት እስከ 25 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጡ፡፡ በዚህም በ13 የክስ መዝገብ ተከሰው የፍርድ ውሳኔ የተላለፈባቸው፡- 1ኛ. ተካ ወ/ማርያም በ25 ዓመት ጽኑ…

የጀርመን መንግስት ለኢትዮጵያ የ56 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግስት በኢትጵያ የምግብ ዋስትናን ጨምሮ ለተለያዩ ዘርፎች የሚውል የ56 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ። ድጋፉ ይፋ የተደረገው የኢትዮ-ጀርመን የልማት ትብብር መድረክ በአዲሰ አበባ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡…