Fana: At a Speed of Life!

በሐምሌ ወር የሰለጠነ የሰው ሃይል ወደ አውሮፓ ሀገራት መላክ ተጀምሯል – ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐምሌ ወር የሰለጠነ የሰው ሃይል ወደ አውሮፓ ሀገራት መላክ መጀመሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡ ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ፤ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕቅድ አፈፃፀም ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎች…

ከ21 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የጤናና የፋይናንስ አመራሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ21 የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ የጤና እና የፋይናንስ አመራሮችና ባለሙያዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ አመራሮችና ባለሙያዎችን የዓድዋ…

ያለ ሐኪም ትዕዛዝ የወባ መድኃኒት መውሰድ ለተለያየ ችግር ይዳርጋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐኪም ያልታዘዘ የወባ መድኃኒትን መውሰድ የተለያዩ ጉዳቶችን እንደሚያስከትል የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ የወባ በሽታ አምጪ ጥገኛ ተኅዋስ ዝርያ ልየታ ሳይደረግና የሕክምና መመሪያ በሌለበት የወባ መድኃኒት መጠቀም÷ ከመድኃኒት መጠን፣ የአወሳሰድ…

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለማልማት የጀመረችውን ጥረት እደግፋለሁ – ቻይና

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሰው ኃይል ልማት በመጀመር የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለማልማት የጀመረችውን ጥረት እንደሚደግፍ የቻይና የኒውክሌር ኃይል ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሊጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በቤጂንግ የሚገኘውን የኒውክሌር ምርመር እና…

ጃክ ሞተርስ በቅርቡ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መገጣጠም ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ (ጃክ ሞተርስ) በቅርቡ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ የመገጣጠም ሥራ ለመጀመር የሚያስችለውን ውሳኔ ማሳለፉን አስታወቀ፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከጃክ ሞተርስ እና ሃዩጃን…

እሁድ ሊካሄድ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን እሁድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ሊደረግ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ተራዘመ፡፡ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሊከናወን ታስቦ የነበረ ቢሆንም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን…

ግለሰብን በማስፈራራትና በመደብደብ ንብረት ወስደዋል ተብለው የተጠረጠሩ የፖሊስ አባላት ፍ/ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሌሊት ለወንጀል መከላከል ሥራ በተሰማሩበት ቦታ ግለሰብን አግተው በሽጉጥ አስፈራርተው ንብረት ወስደዋል ተብለው ስልጣንን ያለ አግባብ መገልገል ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት የፖሊስ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ…

ያልተገባ ዋጋ በሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው ርምጃ እንደሚቀጥል ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርት በሚደብቁና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር አስታወቁ። ተግባራዊ የሆነው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲን ተከትሎ አንዳንድ የንግዱ ማኅበረሰብ…

በክልሉ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 351 የንግድ ተቋማት ታሸጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና ምርት በሸሸጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ እንዳሉት÷ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያን ተከትሎ…

ባንኩ ዛሬ በልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ሸጠ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው ልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር በአማካይ 107 ነጥብ 9 ብር ዋጋ መሸጡን አስታውቋል፡፡ ባንኩ ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የተካሄደውን የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።…