Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ከ2010 የዓለም ዋንጫ በኋላ ምርጥ ብቃቱ የከዳው ቶሬስ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም እግር ኳስ ከተመለከታቸው ምርጥ የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው የስፔን ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ኮከብ ፈርናንዶ ቶሬስ፡፡ ቶሬስ በተጫዋችነት ዘመኑ ከምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን÷ በፍጥነቱ፣ በጎል አስቆጣሪነቱ እና በድንቅ ችሎታው ይታወቃል፡፡ ፈርናንዶ ቶሬስ ለተከላካዮች ፈታኝ ከመሆኑ ባለፈ ጥንካሬው፣ ፍጥነቱ፣ ጉልበቱና የአጨራረስ ብቃቱ አስገራሚ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ቶሬስ ወደ አንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በመጣበት በመጀመሪያው የውድድር ዓመቱ በ33 የሊጉ…
Read More...

መቻል ኢትዮጵያ መድንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቻል ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 አሸንፏል። ቀን 10 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የመቻልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቸርነት ጉግሳ ከመረብ አሳርፏል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው የኢትዮ…

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽረ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽረ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል፡፡ በጨዋታው የምድረ ገነት ሽረ ተጫዋች ስንታየሁ ወለጬ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ…

ቼልሲ ክሪስታል ፓላስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 1 አሸንፏል። አመሻሽ 11፡30 ላይ በክሪስታል ፓላስ ሜዳ በተደረገው ጨዋታ የቼልሲን ግቦች ኤስቴቫኦ፣ ጆአ ፔድሮ እና፣ ኤንዞ ፈርናንዴዝ (በፍጹም ቅጣት ምት) ሲያስቆጥሩ÷ ክሪስ ሪቻርድስ የክሪስታል ፓላስን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።…

ፋሲል ከነማ አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ አርባ ምንጭ ከተማን 3 ለ 2 አሸነፈ። በጨዋታው የፋሲል ከነማን ግቦች ቃልኪዳን ዘላለም (2) እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ ሲያስቆጥሩ÷ የአርባምንጭ ከተማን ግቦች ታምራት ኢያሱ እና ጸጋየ አበራ (በፍጹም ቅጣት ምት) ከመረብ አገናኝተዋል። ቀደም ሲል…

አዳማ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ 0 ለ 0 ተለያይተዋል። ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ነው የተጠናቀቀው። እንዲሁም በአዲስ አበባ ስታዲያም ቀን 10 ሰዓት ላይ የተጀመረው የአርባ ምንጭ…

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል። ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ግቦች እንዳልካቸው ጥበቡ እና ቃለአብ ውብሸት (በራሱ ላይ) አስቆጥረዋል። በጨዋታው ሀዲያ ሆሳዕናን…