Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

ቢዝነስ

የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቡና ንግድ ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የቡና ንግድ ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ የቻይና አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትስስር መማክርት ልዑካን ከኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን እንዲሁም ከቡና ላኪ ድርጅቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡…

በአማራ ክልል ከ16 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት ከ16 ቢሊየን 922 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለጸ። በቢሮው የግብር ትምህርት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ታዘባቸው ጣሴ  እንዳሉት÷ ክልሉ እስከ ኅዳር…

የኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሱዳን የቴሌኮም ግሩፖች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮ ቴሌኮም፣ ጅቡቲ ቴሌኮም እና ሱዳቴል መካከል የሆራይዘን ፋይበር ኢኒሼቲቭ ስትራቴጂያዊ አጋርነት በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል፡፡ የሀገራቱ የቴሌኮም ግሩፖች አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ከፍተኛ አቅም ባለው የፋይበር ኮኔክቲቪቲ ለማስተሳሰር…

አየር መንገዱ አፍሪካን እርስ በርስ የማገናኘት ሚናውን በትጋት እንደሚወጣ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካን እርስ በርስና ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት እየተጫወተ ያለውን የመሪነት ሚና አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡ አየር መንገዱ ወደ ላይቤሪያ ሞንሮቪያ ዳግም በጀመረው የመንገደኞች በረራ ሞንሮቪያ ሲደርስ÷…

ድሬዳዋ እና አላት ነፃ የንግድ ቀጣናዎች በትብብር ለመሥራት ተስማሙ 

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጣና እና የአዘርባጃኑ አላት ነፃ የንግድ ቀጣና በትብብር ለመሥራት ተስማሙ፡፡ ከስምምነት የተደረሰው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የተመራ ልዑክ አላት ነፃ የኢኮኖሚ ዞንን በጎበኙበት ወቅት መሆኑ ተገልጿል፡፡…

በቻይና ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ዐውደ-ርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ምርቶች እየተዋወቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤጂንግ እየተካሄደ በሚገኘው የቻይና ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ዐውደ-ርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ምርቶች እየተዋወቁ ነው፡፡ በዐውደ-ርዕዩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ ላኪዎች እና አቅራቢዎችም እየተሳተፉ…

ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ561 ቶን በላይ ዓሣ ማምረት ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓሣ ምርት የተሠማሩ 22 ማኅበራት ካለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ 561 ነጥብ 5 ቶን የዓሣ ምርት ለአካባቢው እና ማዕከላዊ ገበያ አቀረቡ፡፡ ግድቡ ከኃይል ማመንጨት ባለፈ ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የቤኒሻንጉል…

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል ዘላቂ አገልግሎት ሽልማትን ተቀዳጀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመታዊው የኡጋንዳ “ኢኩላ ቱሪዝም ሽልማት” የ2024 ምርጥ የቢዝነስ ክፍል ዘላቂ አገልግሎት ሽልማትን አሸንፏል። የሽልማት መርሐ ግብሩ በካምፓላ ሸራተን ሆቴል የተካሄደ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ አየር መንገድ…

የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የአሜሪካ ዶላር ግዢ እንዲቋረጥ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የአሜሪካ ዶላር ግዢ ከዛሬ ጀምሮ ማቆሙን አስታወቀ፡፡ የሩሲያ ባንክ እንዳስታወቀው፥ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በሀገር ውስጥ ምንዛሪ ላይ የሚደረጉ የውጭ ምንዛሪ ግዢዎችን የገበያውን ተለዋዋጭነት ለመቀነስ የዶላር…

ዴላሞንት ምግብ ማቀነባበሪያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሥራ ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳዩ ዴላሞት ኢንተርፕራይዝ ምግብ ማቀነባበሪያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የደረቅ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ኢዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር)፤ የኩባንያው…