Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ከአየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) በእስራት እንዲቀጡ ወስኖ  የታሰሩት በቂ ስለሆነ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጠ።…

ስታትስቲክስ ለጠንካራ ፖሊሲ የጀርባ አጥንት ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ስታትስቲክስ መረጃን መሠረት ላደረገ ጠንካራ ፖሊሲ የጀርባ አጥንት ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ። ‎ ‎19ኛው የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የብሔራዊ ስታትስቲክስ የዳይሬክቶሬት ጀነራል ኮሚቴ ዓመታዊ ስብሰባ ‘ፍትህና ካሳ…

የአፍሪካ ኢነርጂ ኤፊሸንሲ ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመጀመሪያው የአፍሪካ ኢነርጂ ኤፊሸንሲ ጉባኤ ከፊታችን ታሕሳስ 1 እስከ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል። የአፍሪካ ኢነርጂና መሰረተ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌራቶ ማታ በሰጡት መግለጫ ÷ የኃይል አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት…

በዛሬው ዕለት ለ30 ሺህ የከተማችን ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጥረናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰጠው ልዩ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለ30 ሺህ የከተማችን ወጣቶችና ሴቶች በዛሬው ዕለት አዲስ የስራ ዕድል ፈጥረናል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንድ ጀምበር ለ30 ሺህ…

አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በፖሊስ ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ ታጠናክራለች – አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ሽብርተኝነትና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ቁርጠኛ ናት አሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከአምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ጋር…

በደሴ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደሴ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል። በከተማዋ ሰኞ ገበያ ክፍለ ከተማ ቢለን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ…

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት በማሳለጥ የጎላ ሚና አለው – አቶ አህመድ ሺዴ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት በማሳለጥ የጎላ ሚና አለው አሉ፡፡ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ሁለተኛው ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን…

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተገማች፣ ግልፅና ምቹ የካፒታል ገበያ ምህዳር መፍጠር አስችሏል – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

‎አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተገማች፣ ግልፅና ምቹ የካፒታል ገበያ ምህዳር መፍጠር አስችሏል አሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)። ሁለተኛው ቀጣናዊ የካፒታል ገበያ ጉባኤ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል እየተካሄደ…

የብልፅግናን ጉዞ ለማፋጠን በአሰሪዎች ተሳትፎና በሠራተኞች መብት መካከል ሚዛን መጠበቅ ወሳኝ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግናን ጉዞ ለማፋጠን የአሰሪዎችን ተሳትፎ በማሳደግና በሠራተኞች መብት አከባበር መካከል ሚዛን መጠበቅ ወሳኝ ነው አሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት…

አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት አቀረቡ

‎አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን አቀረቡ። በዛሬው ዕለት በቃስር አል ዋታን…