Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያውያን ረጅም ዘመናትን በተራመደ የታሪክ ዐሻራ የተሠራን የኅብር ሸማ ነን – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያውያን ረጅም ዘመናትን በተራመደ የታሪክ ዐሻራ የተሠራን የኅብር ሸማ ነን አሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፡፡ የኅብር ቀን "ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት እየተከበረ…

የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ጃሎ እና የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ሁሴን አብዱልቃድር አዲስ አበባ ገብተዋል። የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ በቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለልዑካኑ አቀባበል አድርገዋል፡፡…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-

የኅብር ቀን ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ ኢትዮጵያ በብዙ ጸጋዎች የተሞላች ሀገር ናት፡፡ እነዚህ ጸጋዎቿ የተለያዩ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ ናቸው፡፡ የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክ፣ የሥልጣኔ፣ የእምነት፣ የጾታ፣ የአመለካከት፣ ወዘተ. ብዝኃነት ያለንን የጸጋ ብዛት የሚያመለክት ነው፡፡ ብዝኃነት የኢትዮጵያ…

“ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ እና ዐቅም ነው”

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ እና ዐቅም ነው አለ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፡፡ አገልግሎቱ የኅብር ቀንን አስመልክቶ ያስተላለፈው መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ብዝኃ ማንነት ደምቃ፣ ፀንታና ታፍራ የኖረች፣ ብዝኃ…

በባህርዛፍ የተያዘ መሬትን ወደ ፍራፍሬ ልማት የመቀየር ውጤታማ ተሞክሮ …

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በባህርዛፍ የተያዙ ለም መሬቶችን ወደ ፍራፍሬ ልማት በመቀየር አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ነው አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ…

ምክክር ኮሚሽኑ በካናዳ አጀንዳ ለማሰባሰብ ያዘጋጀው መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ያዘጋጀው መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ እኛ…

የሀገር ዕድገትና ብልፅግና ከግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ውጪ አይታሰብም – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጽኑ መሰረት ላይ የተገነባ የሀገር ዕድገት እና ብልፅግና ከግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ውጪ የሚታሰብ አይደለም አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያን…

የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆኣኦ ሎሬንቾ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንጎላ ፕሬዚዳንት ጆኣኦ ሎሬንቾ በሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማህበረሰብ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል፡፡…

አፍሪካ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለዓለም የሚተርፍ አማራጭ መፍጠር ትችላለች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) አፍሪካ የአየር ንብረት መፍትሄዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለዓለም የሚተርፍ አማራጭ መፍጠር ትችላለች አሉ፡፡ ሁለተኛው የዓለም ዓቀፉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ሳምንት የሚኒስትሮች…

ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት መጎልበት ሚናውን እየተወጣ የሚገኘው የጋራ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ባህልን ለመገንባትና ለመድብለ ፓርቲ ስርዓት መጎልበት የበኩሉን እየተወጣ ነው አሉ። የጋራ ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ጠቅላላ ጉባኤ የ2017…