Browsing Category
የሀገር ውስጥ ዜና
በ2025 የኢትዮጵያ ኤክስፖ የሚሳተፉ አካላት ፕሮፖዛል እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ በሚካሄደው የ2025 የኢትዮጵያ ኤክስፖ ላይ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት ጥናታዊ ጽሑፍ እንዲያቀርቡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጥሪ አቀረቡ፡፡
ከፈረንጆቹ ግንቦት 16…
ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 320 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አወል ሰይድ (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ፤ ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በምርምር ፣ በቴክኖሎጂ…
ዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን እያከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በጅማ እያከበረ ነው፡፡
የመከላከያ ሠራዊት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ሁሉሀገርሽ ደረስ እንዳሉት÷ ሴቶች ከወንዶች እኩል ጀግንነታቸውን አሳይተው በቆራጥነት ኢትዮጵያን…
የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎች የአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት በቅርቡ ግንባታው ተጠናቅቆ ለጎብኝዎች ክፍት የሆነውን የአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ላይ ከጤና ተቋማት የተውጣጡ የጤናው ዘርፍ ሠራተኞች፣ በጎ ፈቃደኞች እና ታዳጊዎች…
የማርሳቤት ክልል አሥተዳዳሪ መህሙድ አሊ በቦረና ገዳ ባሊ ስልጣን ርክክብ ላይ ለመታደም ያበሎ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማርሳቤት ክልል አሥተዳዳሪ መህሙድ አሊና የኬንያ ልዑካን ቡድን አባላት በ72ኛው የቦረና ገዳ ባሊ ስልጣን ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመታደም ያበሎ ከተማ ገብተዋል፡፡
ልዑካኑ ያበሎ ከተማ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል መባሉን የኦሮሚያ…
ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ማፍረስ እንደማይቻል ማረጋገጥ ተችሏል- አቶ አረጋ ከበደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በተወሰደው ሕግ የማስከበር ርምጃ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ማፍረስ እንደማይቻል ማረጋገጥ ተችሏል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ገለፁ፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአማራ ክልል ተመራጮች ከክልሉ ምክር ቤት…
የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት የላቀ አስተዋጽዖ አበርክተዋል- ፕሬዚዳንት ታዬ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት እና የኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ አስተዋጽዖ ማበርከታቸውን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው፤ ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ…
በ6 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ በረራ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ከምሽቱ 5 ሠዓት ጀምሮ በሥድስት ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ በረራ ማድረጉ ተገለጸ፡፡
ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኤርናቪጌሽን አገልግሎት ዘርፍ እነዚህን ሥድስት…
አካዳሚው ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ70ኛ ዙር ቃኘው ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው፡፡
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ጄኔራል መኮንኖች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ…
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች እየተከበረ መሆኑን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ዕለቱ የሚከበረው “ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል” በሚል መሪ ሐሳብ መሆኑን…