Browsing Category
ስፓርት
ሀዋሳ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢንያም በላይ የሀዋሳ ከተማን ማሸነፊያ ግብ…
ሲዳማ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን በማሸነፍ የ2017 የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸንፏል።
የሲዳማ ቡናን ግቦች ሀብታሙ ታደሰ እና መስፍን ታፈሰ…
18ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መነሻውንና መድረስ በመስቀል አደባባይ ያደረገው 18ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ፋንቱ ወርቁ እና በወንዶች ሌሊሳ ፉፋ አሸንፈዋል።
ውድድሩን በሴቶች ፋንቱ ወርቁ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በበላይነት ስታጠናቅቅ÷ ውድድሩን ለመጨረስ 1 ሰዓት…
የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ፖርቹጋል ከስፔን ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት የፍጻሜ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ላይ በሙኒክ አሊያንዝ አሬና ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን÷ ሁለቱ ቡድኖች ካላቸው ምርጥ ተጫዋቾች አንጻር አጓጊ ሆኗል፡፡…
ቶተንሀም ሆትስፐር አንጂ ፖስቴኮግሉን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐር የክለቡን አሰልጣኝ አንጂ ፖስቴኮግሉን አሰናብቷል፡፡
አሰልጣኙ በስፐርስ በነበራቸው የሁለት ዓመት ቆይታ የዩሮፓን ሊግ ዋንጫን አሳክተዋል፡፡
በፖስቴኮግሉ የተመራው ቶተንሀም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት…
ራፊንሀ -የስፔን ላሊጋ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጫዋች ራፊንሀ የ2024/25 የውድድር ዓመት የስፔን ላሊጋ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል፡፡
ራፊንሀ በውድድር ዘመኑ ለባርሴሎና 36 የላሊጋ ጨዋታዎችን በማድረግ 18 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡…
አርሰናል የጋብሬል ማግሀሌስን ውል አራዘመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን ጋብሬል ማግሀሌስን ውል እስከ ፈረንጆቹ 2029 ማራዘሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ብራዚላዊው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች ጋብሬል ማግሀሌስ ከአምስት ዓመት በፊት ከሊል ወደ አርሰናል መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡
ማግሀሌስ…
መቐለ 70 እንደርታ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ሲዳማ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 9 ሠዓት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቤንጃሚን ኮቴ የመቐለ 70 እንደርታ ማሸነፊያ…
ሐዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ለሐዋሳ ከተማ አሊ ሱሌማን አራት ግቦችን ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ጎል ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሐዋሳ ከተማው…