Fana: At a Speed of Life!

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) የዜጎችን ማህበራዊ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚሰሩ ተግባራት እንዲጠናከሩ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በክረምት በጎ ፈቃድ አግልግሎት የዜጎችን ማህበራዊ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚሰሩ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር አሳሰቡ፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል…

በፈረንሳይ የተቀሰቀሰው ግጭት እና ሁከት ተባብሶ መቀጠሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፖሊስ በአንድ ወጣት ላይ የፈፀመውን ግድያ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ግጭት እና ሁከት ተባብሶ መቀጠሉ ተስምቷል፡፡ ግጭቱ አንድ የፖሊስ ኦፊሰር የአልጀሪያ ዜግነት ያለውን የ17 ዓመት ወጣት "ትራፊክ ጥሶ አልፏል" በሚል ተኩሶ መግደሉን ተከትሎ…

ኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሟትም ስኬቶችንም አስመዝግባለች- ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ2015 ዓ.ም ከውስጥና ከውጪ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሟትም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቧን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ የፌዴራል እና የክልል የሚዲያና…

በጸጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍተው ነበር የተባሉ 20 ተጠርጣሪዎች ላይ ለምርመራ ማጣሪያ የ14 ቀን ጊዜ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በመያዝ በፀጥታ አካላት ላይ ተኩስ ከፍተው ነበር የተባሉ 20 ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ማጣሪያ እንዲደረግ የ14 ቀን ጊዜ ፈቅዷል፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በመርማሪ…

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ብቁ የሰው ኃይል ለመፍጠር በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ብቁ የሰው ኃይል፣ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር አቅዶ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ፡፡ የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የምርታማነት የምክክር መድረክ…

የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭትን በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርና ሚኒስቴር በ2015/16 የምርት ዘመን የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ከክልል ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው። በመድረኩ የኦሮሚያ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮዎች ማዳበሪያ የሚያጓጓዙ…

የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ ነገ በአሶሳ ከተማ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ንቅናቄ ነገ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ እንደሚጀመር የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ አስታወቀ፡፡ የሊጉ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አባንግ ኩመዳን በሰጡት መግለጫ…

ሙስናን በሐቀኝነት እንጂ በማስመሰል ልንዋጋው አንችልም – ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሙስናን በሐቀኝነት እንጂ በማስመሰል ልንዋጋው አንችልም ሲሉ የሥነ -ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላት የሥነ-ምግባር ክትትል እና የጥቅም ግጭትን ለመከላከልና ለማስወገድ…

ኢትዮጵያ በ3ኛው የቻይና-አፍሪካ የንግድ እና ኢኮኖሚ ኤክስፖ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በ3ኛው ቻይና-አፍሪካ የንግድ እና ኢኮኖሚ ኤክስፖ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡ በቻይና ሁናን እየተካሄደ በሚገኘው ኤክስፖ ላይ የ53 አፍሪካ ሀገራት ተወካዮች እና የበርካታ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች አመራሮች…

አገራዊ እሴቶች ለብሔራዊ መግባባት ያላቸውን አበርክቶ የሚዳስስ መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ እሴቶች ለብሔራዊ መግባባትና ለአገር ግንባታ ያላቸውን አበርክቶ የሚዳስስ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ "አገራዊ እሴቶች ለብሔራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ የሚገኘው መድረክ÷ በሰላም ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ…