Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ መሆኗ ለቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ስበት የጎላ አስተዋጽኦ አለው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ መሆኗ ለቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ስበት የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ምሁራን ገለጹ፡፡ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪና መምህሩ ዱጋሳ ሙሉጌታ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር…

የሀገር አቀፍ ሕግ አውጪዎች የጋራ የምክክር መድረክ በሐረር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር አቀፍ ሕግ አውጪዎች የጋራ የምክክር መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ ቤት ፕሬዚዳንት…

በመዲናዋ ከበዓላት ጋር በተያያዘ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለገና (ልደት) እና ጥምቀት በዓላት የኢንዱስትሪ እና የግብርና ምርቶች አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በልዩ ትኩረት የተቀናጀ ስራ እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት…

በአማራ ክልል 487 ቢሊየን ብር ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 487 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡ 1 ሺህ 12 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ገለጸ። የቢሮው ሃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት÷ በክልሉ በተለያዩ…

አብሮነትን በዘላቂነት ለመገንባት አስተሳሳሪ ትርክቶችን መገንባት ያስፈልጋል – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እንደ ሀገር አብሮነትን በዘላቂነት ለመገንባት አስተሳሳሪ ትርክቶችን መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለጹ፡፡ "ብዝሃነትን መኖር” በሚል መሪ ሃሳብ ሀገር አቀፍ የአብሮነት ቀን በመከበር ላይ ይገኛል።…

ለበዓል ገበያ የምርት እጥረት እንዳይኖር በቅንጅት እየተሠራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለገና (ልደት) እና ጥምቀት በዓላት አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በዓላቱን ታሳቢ ያደረገ መነሻ ዕቅድ ተዘጋጅቶ÷ ለዋጋ ንረት…

በኦሮሚያ ክልል ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የውኃ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት በቅተዋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከ500 ሺህ በላይ ወገኖችን መድረስ የቻሉ 2 ሺህ 618 የውኃ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን የክልሉ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ መሐመድ ኑራ (ኢ/ር) ለፋና…

ጋናዊቷ ከ5 ቀናት በላይ ሳታቋርጥ በማዜም የዓለም ክብረ-ወሠን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አፉዋ አሳንቴዋ ኡዉሱ አዱዎነም የተባለች ጋናዊት ዘፋኝ የዓለም ክብረ-ወሠን ለመስበር ከአምስት ቀናት በላይ ያለማቋረጥ ማዜሟ ተነግሯል፡፡ አፉዋ አሳንቴዋ ÷ “ሲንግ ኤ ቶን” በሚል ርዕስ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና ዋና ከተማ አክራ ያለማቋረጥ…

ከፍተኛ የሃማስ ባለሥልጣን መገደሉ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሳሌህ አል አሮሪ የተባለ የሃማስ ከፍተኛ ባለሥልጣን በቤይሩት በደረሰ ፍንዳታ መገደሉ ተገለጸ፡፡ አል አሮሪ ÷ የአንድ የሃማስ ወታደራዊ ክንፍ መሥራች እና የቡድኑ የፖለቲካ ቢሮ ምክትል መሪ እንደነበር ስካይ ኒውስ አስነብቧል፡፡ አል አሮሪ…