Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን የቢዝነስ ጀት አውሮፕላን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተረከበው ቦይንግ 737-800 የተሰኘ የቢዝነስ ጀት አውሮፕላን ልዩ አገልግሎት ለሚሹ ደንበኞቹ እንደሚውል ተጠቁሟል። ከዚህ ቀደም ለልዩ በረራዎች የሚውሉ አገልግሎቶችን በመደበኛ አውሮፕላኖች ሲሰጥ መቆየቱን የኢትዮጵያ…

ለልማት ሥራ በሕጉ መሠረት መሬት ለጠየቁ አካላት እንዲሰጣቸው ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ አሥተዳደር የልማት ሥራ ለማከናወን በሕግና መመሪያ መሠረት መሬት ለጠየቁ አካላት ተዘጋጅቶ የተቀመጠው መሬት እንዲሰጣቸው ውሳኔ ተላለፈ፡፡ የአሥተዳደሩ ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ መሬትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔዎችን…

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ያዘጋጁልን ኢፍጣር ኢትዮጵያ ለስደተኞች ያላትን ክብር ያሳየ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያዘጋጁልን የኢፍጣር መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ለስደተኞች ያላትን ክብር በተግባር ያሳየ ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የተለያዩ ሀገራት ስደተኞች ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ የተለያዩ…

የታንዛኒያ የመከላከያ ኃላፊዎች የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደርን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታንዛንያ ከፍተኛ የመከላከያ ኃላፊዎች የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደርን ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸውም፤ የተቋሙን የታለንት ልማት ማዕከል፣ በራስ ዐቅም የለሙ የመረጃና ኮሙኒኬሽን እንዲሁም ሌሎች አስቻይ የቴክኖሎጂ ምርትና አገልግሎቶችን…

በሲዳማ ክልል ለምርት ዘመኑ 300 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ይቀርባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል ለ2017/18 የምርት ዘመን ጥቅም ላይ የሚውል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እየቀረበ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል። የቢሮው ምክትልና የግብርና ግብአት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ለገሰ ሀንካርሶ እንዳሉት፤…

ኢትዮጵያ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ውህደት የሚያሳልጡ መሰረተ ልማቶችን እየዘረጋች ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ውህደት የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደምትገኝ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ። የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 57ኛው አህጉራዊ የፋይናንስና ምጣኔ ሃብት የሚኒስትሮች ጉባዔ…

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት – የባሕር ዳር ልምድ

ዛሬ የባሕርዳርን ከተማ የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ ተመልክቻለሁ። ተፈጥሮ እና የሰው ጥበብ ተዋሕደው ባሕርዳርን ይበልጥ ውበቷን እያወጡት ነው። ከተማዋን የንግድና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አመራሩ ከሚያደርገው ጥረት የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ። 1. ባሕር ዳር በፈተና ውስጥ…

በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 53 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያኑ ከማይናማር እገታ ወጥተው ታይላንድ ወታደራዊ ካምፕ…

በሞጆና አዳማ ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን የኃይል መቆራረጥ የቀነሰ ሥራ መሰራቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞጆና አዳማ ከተሞች የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን የኃይል መቆራረጥ የቀነሰ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ሥራ መሰራቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዳማ ሪጅን አስታወቀ። በከተሞቹ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የሚቀርበውን የኃይል አቅርቦት…

አንጋፋው አርቲስት መርዓዊ ስጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው መርዓዊ ሥጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ክላርኔት በመጫወት የሚታወቀው አርቲስት መርዓዊ፤ ከሙዚቀኛነቱ ባለፈ በትወና መድረክ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሏል፡፡ አርቲስት መርዓዊ ስጦት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ…