Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበት የመግባቢያ ሥምምነት በመፈረሙ ተቋማት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ከሶማሊላንድ ጋር መፈራረሟ ተከትሎ የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ…

እንደ ሀገር ገዥ ትርክትን በማስረጽ ብሔራዊነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ ገዥ ትርክትን በማስረጽ ብሔራዊነትን ማጎልበት ለብልጽግና ጉዞ ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ ዓለማየሁ ባውዲ ገለጹ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የተከለሰ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ…

ሀገር አቀፍ የሰላም ፎረም ጥምረት ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ሂደትን ውጤታማ ማድረግ ያስችላል የተባለ ''ሀገር አቀፍ የሰላም ፎረም ጥምረት'' ተመሰረተ። ጥምረቱን ለመመስረት የተዘጋጀ መድረክ በአዳማ ከተማ የተካሄደ ሲሆን፥ በመድረኩ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ…

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የባሕር በር በምታገኝበት የመግባቢያ ሥምምነት ዙሪያ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ምን አሉ?

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን ሥምምነት ከሶማሊላንድ ጋር መፈራረሟን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብዙኃን መገናኛዎች ሥምምነቱን እና የባሕር በር ጥያቄን የተመለከቱ መረጃዎች አውጥተዋል፡፡ በተመሳሳይ ዓለም አቀፍ ብዙኃን መገናኛዎችም…

የሐይማኖት አባቶች የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ የጎላ ሚና እንዳላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐይማኖት አባቶች የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ የጎላ ሚና እንዳላቸው የገቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ሚኒስቴሩ ከሐይማኖት አባቶች ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡ በውይይት መድረኩ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴም ባደረጉት…

ኢትዮጵያ የባህር ወደብ ተጠቃሚ የሚያደርጋትን ስምምነት መፈረሟ ፍትሃዊ ተጠቃሚነቷን የሚያረጋግጥ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባህር ወደብ ተጠቃሚ የሚያደርጋትን ስምምነት መፈረሟ ፍትሃዊ ተጠቃሚነቷን የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ተመስገን ዲሳሳ (ዶ/ር) እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ተናገሩ፡፡…

ብሄራዊ የተቀናጀ የውኃ ሀብት አስተዳደር ፕሮግራምን በሚመለከት ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሄራዊ የተቀናጀ የውኃ ሀብት አስተዳደር ፕሮግራም እና በሌሎች የውኃ ሀብት አስተዳደርን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከክልሎች የውኃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊዎችና የውኃ ሀብት አስተዳደር የሥራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት እተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ የውኃና…

“የምስራቅ አፍሪካ አርብቶአደሮች ኤክስፖ” በጥር ወር ይካሄዳል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) "የምስራቅ አፍሪካ አርብቶአደሮች ኤክስፖ" ከጥር 17 እስከ ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና የቆላማ አካባቢዎችን የልማት…

በጃፓን በተከሰተ ርዕደ መሬት የሟቾች ቁጥር 30 መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን በተከሰተ ርዕደ መሬት በትንሹ 30 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል፡፡   ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ የነፍስ አድን ሰራተኞች በፍርስራሽ ውስጥ የታፈኑ ሰዎችን በህይወት ለማዳን እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።  …

በሲዳማ ክልል 31 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ጥራትና አግባብነት ባልተከተለ መልኩ ከደረጃ በታች ሲያሰለጠኑ በተገኙ 31 የግል የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ተገለጸ፡፡ የክልሉ የስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ ሀገረ ጽዮን አበበ፥ ቢሮው…