Fana: At a Speed of Life!

ፋና የስልጠና ማዕከል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሥልጠና ማዕከል ዕውቅና ባገኘባቸው አራት የሙያ መስኮች መደበኛ ስልጠና መስጠት መጀመሩን ዛሬ አብስሯል። ማዕከሉ ከዚህ ቀደም በጋዜጠኝነት፣ በሚዲያ ኮሙኒኬሽን እና በሚዲያ ቴክኖሎጂ የስልጠናና የማማከር ስራ ሲሰራ ቆይቷል።…

ፓኪስታን ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው የኢኮኖሚ ዕድገት ለሌሎች አርአያ መሆን እንደሚችል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር የውጭ ግንኙነት ልዩ አማካሪ ሰይድ ታሪቅ ፋጢሚ ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም በሀገራቱ ሰላም፣ ብልጽግና እና የዘላቂ ልማት የጋራ ግቦችን ለማሳካት የባለብዙ…

የአሜሪካና ሩሲያ የሁለትዮሽ ውይይት በኢስታንቡል መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁለተኛው ዙር የአሜሪካ እና ሩሲያ ውይይት በቱርክ ኢስታንቡል መካሄድ ጀምሯል፡፡ በአሜሪካ የሩሲያ አምባሳደር አሌክሳንደር ዳርኪቭ እና በአሜሪከ ረዳት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሶናታ ኮልተር አማካኝነት የተመሩት የሁለቱ ሀገራት ልዑካን ቡድኖች…

ኮሚሽኑ አሳታፊና አካታች የሀሳብ ውክልና እንዲኖር እየሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አሳታፊና አካታች የሀሳብ ውክልና እንዲኖር እየሰራ መሆኑን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ገለጹ። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ…

ለጋምቤላ ከተማ ኮሪደር ልማት ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ከተማ የኮሪደር ልማት የገቢ ማሰባሰቢያ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ በተገኙበት እየተካሄደ ነው። የጋምቤላ ከተማ የኮሪደር ልማት የመጀመሪያው ምዕራፍ እየተከናወነ ሲሆን÷ በልማቱ ሕዝቡን ተሳታፊ ለማድረግ…

የአማራ ክልል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል አጀንዳ የማሠባሠብ ሥራውን እያከናወነ ነው። የወረዳ ማኅበረሰብ ተወካዮች የአጀንዳ ማሠባሠብና ለአጠቃላይ የምክክር ጉባዔው ወኪሎችን የመምረጥ ሥራ ሚያዝያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል።…

ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት❗️

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንተርኔት አጠቃቀም በየቀኑ እየጨመረ በሄደበት በዚህ ዘመን፣ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስጋቶችም እየተስፋፉ ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቅርቡ በርካታ አደገኛ የኢንተርኔት አድራሻዎችን (URLs) መርምሮ፣ እነዚህ…

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ በተለያዩ ዘርፎች ከተሰማሩ የቱርክ ኩባንያዎች ተወካዮችና ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡…

የግብርና መሠረታዊ ምርት 45 በመቶ ከእንስሳት ሀብት ዘርፍ እየመነጨ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብት በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ሀገራት ውስጥ እንደምትገኝ እና ዘርፉም ከአጠቃላይ ግብርና መስክ 45 በመቶ እያበረከተ መሆኑን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ የሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ የከተሞች መስፋፋት፣ የወተትና ወተት…

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ለአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት የእንኳን ደህና መጣቹህ አቀባበል አደረጉ፡፡ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ የሴራሊዮን ቀዳማዊት እመቤት ፋቲማ ማዳ…