Fana: At a Speed of Life!

በሠመራ ለሚገነባው የወንጀል ምርመራ ቢሮ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ ለሚያስገነባው የወንጀል ምርመራ ቢሮ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡ የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት÷ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና የሠመራ ከተማ ከንቲባ አብዱ ሙሳ ናቸው፡፡…

አሜሪካ በኢራቅ እና ሶሪያ ሚሊሻዎች ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከቀናት በፊት በዮርዳኖስ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ለተገደሉባት ወታደሮቿ የመጀመሪያውን አፀፋ በኢራቅ እና ሶሪያ በሚገኙ ሚሊሻዎች ላይ ሰነዘረች፡፡   የዓየር ድብደባ ጥቃቱ የተሰነዘረው በሰባት ቦታዎች ከ85 በሚልቁ ኢላማዎች…

በጋራ ጥረታችን የጀመርነው ሥራ ፍጥነቱን ጠብቆ እንዲሄድ እንረባረብ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና አቅማችንን በምሉዕ ለመጠቀም በጋራ ጥረታችን የጀመርነው ሥራ ፍጥነቱን ጠብቆ እንዲሄድ መረባረብ ይገበል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷የወቅቱ…

የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባሕር ዳር ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ ዛሬ ባሕር ዳር ገብቷል፡፡ የልዑካን ቡድኑም÷ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴን፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበልን፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ…

የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀናት የሚቀየው የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡ ኮሚቴው በሦስት አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን÷ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮችንም በአብላጫ ድምፅ በማፅደቅ ስብሰባው…

በጣሊያን ኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈው ሰርከስ ቡድን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ተመዘገበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን በተካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈው የብላክ ላየን ሰርከስ ቡድን የዓለምን ክብረ ወሰን በመስበር በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ተመዝግቧል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ÷ የዓለምን ክብረ ወሰን በመስበር…

ሰላም እንዲረጋገጥ የሰላም ሰራዊት አባላት ከፍተኛ ሥራ ማከናወናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ቀጣይነት ያለው ሰላም እንዲረጋገጥ የሰላም ሰራዊት አባላት ያከናወኑት ሥራ ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ በከተመዋ የተካሄዱ ሐይማኖታዊ እና የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ አስተዋጽኦ…

በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ልማትና አብሮነት ላይ ያተኮረ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ የሰላም ግንባታ፣ ዘላቂ ልማትና አካባቢያዊ አብሮነት ላይ ያተኮረ ጉባዔ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው። ጉባዔው "ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሶማሊ ላንድ መካከል ቀጣናዊ ትስስርን ለመፍጠር፣ ለሰላም…

ዛሬ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲካሄዱ ማሊ ከኮትዲቯር እንዲሁም ኬፕ ቨርዴ ከደቡብ አፍሪካ ይገናኛሉ፡፡ ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረገው ፍልሚያ ማሊ ከአስተናጋጇ ኮትዲቯር ምሽት 2፡00 ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን…

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ እጩ መኮንኖችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለ24ኛ ዙር በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን የአንድነት ኮርስ እጩ መኮንኖችን አስመርቋል፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የድሬዳዋ ከተማ…