Fana: At a Speed of Life!

ኢስተርን ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤቶችን መገንባት እንደሚፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ኢስተርን ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለመገንባትና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የትራንስፎርሜሽንና ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ…

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ቡድን ያወጣውን ሪፖርት ውድቅ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰብአዊ መብቶች ጉዳይን እንዲመረምር የተሰየመው ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ባለሙያዎች ቡድን በ54ኛው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ያቀረበውን ሪፖርት ኢትዮጵያ እንደማትቀበለው አስታውቃለች። በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የኢፌዲሪ ቋሚ…

በባህርዳር ከተማ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላም ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር "ሁለንተናዊና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት የሁሉንም አካል ርብርብ ይጠይቃል" በሚል መሪ ሃሳብ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላምና የልማት ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይት መድረኩ የባህር ዳርና አካባቢው…

በአፋር የቱሪዝም ሃብትን በማልማትና በማስተዋወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ያለውን የቱሪዝም ሀብት በማልማትና በማስተዋወቅ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የዓለም ቱሪዝም ቀንን ምክንያት በማድረግ በክልሉ ያሉ የቱሪዝም ሃብቶችና ባህሎችን የማስተዋወቅ…

ፒሮላ የተሰኘ አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፒሮላ የተባለ አዲስ የኮቪድ-19 ዝርያ በኒውዝላንድ ቆሻሻ ውሃ ውስጥ መገኘቱ ተገለጸ፡፡ ቫይረሱ ከፈረንጆቹ ሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሥርጭቱን ሳይጀምር አልቀረም ተብሏል፡፡ የዘርፉ አጥኚዎች ቢኤ.2.86 የሚል መጠሪያ…

9ኛው አፍሪካ አቀፍ የወባ ትንኝ ቁጥጥር ማኅበር ጉባዔ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 9ኛው አፍሪካ አቀፍ የወባ ትንኝ ቁጥጥር ማኅበር ዓመታዊ ጉባዔ እና ዐውደ - ርዕይ ተጠናቀቀ፡፡ ጉባዔው "በበሽታ ተኅዋስያን ላይ ከሚታዩ ሥጋቶች አንፃር ክትትልን እና ቁጥጥርን ማስተካከል"…

በኢትዮጵያና አልጄሪያ መካከል የቀጥታ የአውሮፕላን በረራ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና በአልጄሪያ መካከል የመጀመሪያው የቀጥታ በረራ ተደርጓል፡፡ የቀጥታ በረራውን በአልጀሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአልጀርስ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ከአልጄሪያ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዮሴፍ ቸርፋ እና…

አሜሪካ 500 ሺህ ለሚደርሱ የቬኒዝዌላ ፍልሰተኞች የሥራ ፈቃድ ሰጠች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ከፈረንጆቹ ነኀሤ ወር በፊት ድንበር አቋርጠው ለገቡ 500 ሺህ ያኅል የቬኒዝዌላ ፍልሰተኞች የሥራ ፈቃድ ሰጠች፡፡ የባይደን አስተዳደር ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በበርካታ የቬኒዝዌላ ጥገኝነት ጠያቂዎች በመጨናነቁ መሆኑን ብሉምበርግ…

ፊፋ የአፍሪካ ሀገራትን ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊፋ የካፍ ዞን የአፍሪካ ሀገራትን ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚሁ የፊፋ ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በካፍ እውቅና ስር ከሚገኙ 50 ሀገራት 42ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ከዓለም ደግሞ 142ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ሞሮኮ…

ሉሲዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታውን ቀን 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ያካሂዳል ። በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ÷ 26 ተጫዋቾችን በመያዝ ዝግጅቱን…