Fana: At a Speed of Life!

ታጥቀው ጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀበሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በአንካሻ ገብርኤል ቀበሌ ታጥቀው ጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀበሉ፡፡ በቀጣናው በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመራው ኮማንድ ፖስት ባደረገው የተቀናጀ ሥራ በጫካ…

ከአየር መንገዱ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል ላይ የምስክር ቃል መሰማት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ላይ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ቃል መሰማት ተጀመረ። የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር…

አየር መንገዱ ወደ ደምቢዶሎ የሚያደርገውን በረራ አሳደገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደምቢዶሎ የሚያደርገውን በረራ ከሕዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከአዲስ አበባ ዕለታዊ በረራ የሚጀምር መሆኑን አብስሯል፡፡ በዚህም አየር መንገዱ ለደንበኞቹ በድረ-ገፅ www.ethiopianairlines.com…

 ጓርዲዮላን ምን ነካቸው?

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የእግር ኳስ ሊቅ አሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ ከትናንቱ ጨዋታ በኋላ ጭንቅላታቸውን እና አፍንጫቸውን በጥፍራቸው መቦጫጨራቸው አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ በውድድር ዓመቱ ማንቼስተር ሲቲ እያሳየ ባለው ደካማ እንቅስቃሴ ምክንያት ከተጫዋቹ ጋር እሰጣገባ…

አቶ ደስታ ሌዳሞ በኩታገጠም የለማ የቢራ ገብስን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን ጤጥቻ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የቢራ ገብስ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡ የጉብኝቱ ዓላማ የመኸር እርሻ ልማት እንቅስቃሴ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለመገምገም መሆኑም ተመላክቷል። በዞኑ…

 በሶማሊያ የሚደረገው የአትሚስ የሃይል ስምሪት የቀጣናው ደህንነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሆን አለበት – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) ቀጣይ የሃይል ስምሪት የቀጣናውን ደህንነት በሚያረጋግጥ መልኩ መሆን እንደሚገባው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁራን አስገነዘቡ። ስምሪቲ በጥንቃቄ ካልተመራ በምስራቅ አፍሪካ…

በግብርና ሜካናይዜሽን የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶችን በግብርናው ዘርፍ ማሳተፍ ለተሻለ ምርታማነት ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው የኢትዮጵያ ግብርና መሐንዲሶች ማህበር ገለጸ፡፡ በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት ያለመው የኢትዮጵያ ግብርና መሐንዲሶች ማህበር ዓመታዊ ኮንፈረንስ ተካሂዷል፡፡…

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለትምህርት አመራሮች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለትምህርት ቤት አመራሮች የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዋቼሞ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን በስልጠናው ማስጀመሪያ…

የኢትዮጵያ አየር ሃይል 89ኛ የምስረታ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ሃይል 89ኛ የምስረታ በዓል በተለያዩ መርሐ-ግብሮች ተከበረ፡፡ በዓሉን አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ አየር ሃይል ፎረም ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እንደተናገሩት፤ የሀገር…

ዴላሞንት ምግብ ማቀነባበሪያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሥራ ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳዩ ዴላሞት ኢንተርፕራይዝ ምግብ ማቀነባበሪያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የደረቅ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ኢዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ(ዶ/ር)፤ የኩባንያው…