Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል የ2018 በጀት 400 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ 400 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ሆኖ የቀረበለትን የክልሉን የ2018 በጀት አጽድቋል፡፡ ጨፌ ኦሮሚያ በ6ኛ የስራ ዘመን 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባዔ ሁለተኛ ቀን ውሎው የክልሉን የ2018 በጀት እና የ2017 ተጨማሪ በጀት…

ከ121 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የዋካ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን በ121 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የዋካ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል። በሆስፒታሉ ምረቃ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)…

ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎትን የሚሰጥ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት እየተሰራ ነው – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የሕግ የበላይትን የማረጋገጥ እና ጥራት ያለው የዳኝነት አገልግሎትን የሚሰጥ የፍትሕ ሥርዓት ለመገንባት እየተሰራ ነው አሉ። የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕንጻ እና የዲጂታላይዜሽን ምረቃ…

በፍትሕና ዳኝነት ዘርፍ በተሰሩ የሪፎርም ሥራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን ማጠናከር ይገባል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፍትሕ እና ዳኝነት ዘርፍ በተሰሩ የሪፎርም ሥራዎች የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ፡፡ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕንጻ እና የዲጂታላይዜሽን ምረቃ ሥነ ሥርዓት በባሕርዳር…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት አዋጆችንና ደንቦችን በማጽደቅ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 5ኛ መደበኛ ጉባዔ የተለያዩ አዋጆችንና ደንቦችን በማጽደቅ ተጠናቅቋል፡፡ ምክር ቤቱ የክልሉን ሕዝቦች ተጠቃሚነት ይበልጥ በሚያረጋግጥ አግባብ የተዘጋጁ ረቂቅ አዋጆችንና ደንቦችን ነው መርምሮ ያጸደቀው፡፡…

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡ ከ18 ዓመት በታች 5 ሺህ ሜትር ሴቶች ርምጃ የፍጻሜ ውድድር አትሌት ሕይወት አምባው ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡…

የኦሮሚያ ክልል የልዩ አዳሪና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የትምህርት ፌስቲቫል እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 3ኛው የኦሮሚያ ክልል የልዩ አዳሪ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፌስቲቫል በአዳማ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡ የትምህርት ፌስቲቫሉን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች…

በሌማት ትሩፋት 326 ሺህ ቶን ማር ተመረተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር 326 ሺህ ቶን ማር ተመርቷል አለ የግብርና ሚኒስቴር፡፡ የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ የሌማት ትሩፋት ለማር ምርት መሻሻል…

በቬይትናም የቱሪስት ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ የ37 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቬይትናም የቱሪስት ጀልባ ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የ37 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ አደጋው በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘውና የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው ሃ ሎንግ ቤይ ነው የተከሰተው፡፡ አብዛኛዎቹ ተሳፋሪዎች ከዋና ከተማዋ ሃኖይ…

በኦሮሚያ ክልል ሙያዊ ግዴታቸውን ባልተወጡ 394 ዳኞች ላይ ርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የዳኝነት ሥርዓት በጎደላቸው 394 ዳኛዎች ላይ ርምጃ ተወስዷል አለ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ገዛሊ አባሲመል በ6ኛው ጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ እንዳሉት ÷ በ2017 በጀት ዓመት…