Fana: At a Speed of Life!
Browsing Category

የሀገር ውስጥ ዜና

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በጁገል ቅርስ ያለማው መንገድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፉ የጁገል ቅርስ ያለማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ የሀረሪ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በክልሉ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ምቹ…

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን ማህበር ሊመሰረት ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሚያከናውናቸው ሀገራዊ ተግባራት ላይ የቀድሞ ምሩቃን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ማህበር ሊመሰረት ነው፡፡ የጎንደር ዩንቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ቀናት…

በኦሮሚያ ክልል 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር ለዘር ዝግጁ ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል በመኸር እርሻ እስካሁን 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር መሬት ለዘር ዝግጁ ተደርጓል አለ የክልሉ ግብርና ቢሮ፡፡ የቢሮው ም/ሃላፊ አቶ በሪሶ ፈይሳ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት ÷ በክልሉ ለመኸር እርሻ አስፈላጊው ዝግጅት…

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ በአግባቡ እንዲከፈል ክትትል እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የጡረታ መዋጮ በአግባቡ እንዲከፈል አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ ነው አለ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር፡፡ የአስተዳደሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አባተ ምትኩ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ የግል…

የብልፅግና ፓርቲ መመስረት ለሀረሪ ክልል ዕድገት ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ መመስረት ሀረሪ ክልልን ከኋልዮሽ ጉዞ በመግታት ዕድገት እንዲመዘገብ አስችሏል አሉ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፡፡ አቶ አደም ፋራህ በሀረሪ ክልል በዘጠኙም ወረዳዎች የተገነቡ የፓርቲ ጽ/ቤቶችን መርቀው…

በጉዳያ ቢላ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉዳያ ቢላ ወረዳ ኢፈ ቢያ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ አደጋው መጠጥ የጫነ ኤፍኤስአር ተሽከርካሪ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ወደ ባኮ ከተማ ሲጓዝ በመገልበጡ ነው የተከሰተው፡፡ በተፈጠረው…

ምክር ቤቱ የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አጸደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ነው የተሻሻውን አዋጅ ያጸደቀው። በምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች…

ከፍተኛ ዕውቀት፣ ሀብትና ልምድ የተገኘበት ህዳሴ ግድብ …

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ሂደት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ዕውቀት፣ ሀብትና ልምድ ያመጣ ፕሮጀክት ነው። በመጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ግንባታው በይፋ የተጀመረው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች የተሳተፉ…

የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅ ፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጅን አፀደቀ። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባ ያፀደቀው የተሻሻው አዋጅ በቀጣይ ዓመት ለሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ 26 አንቀፆች…

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት 3ኛ አመት 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የጠቅላላ ጉባኤ አባላት በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጂ…