Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ36 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተያዘው የክረምት ወቅት ከ36 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ሃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፥ የክረምት ችግኝ ተከላ በይፋ ከተጀመረበት አንስቶ…

በኦሮሚያ ክልል 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መተከሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እስካሁን በ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ሔክታር መሬት ላይ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ መተከሉን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡ የመርሐ ግብሩን ዕቅድ ለማሳካት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በተከናወኑ ተግባራት…

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በጸዳ መልኩ መሰጠቱን አንስተዋል፡፡ በፈተና ወቅት…

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ 100 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በፖሊስ አባላት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከነ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የጨፌ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አባላት…

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከ56 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከ56 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ። የደቡብ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ እየተካሔደ ነው።…

አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር (ዶ/ር) ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያዩ። በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት፣…

በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱት የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ወደ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የአልባሳት ግዢ ጋር ተያይዞ በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱ የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ተጠርጣሪዎቹ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ…

በኦሮሚያ ክልል በ2016 በጀት ዓመት ከ265 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት ከ265 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ በሰጡት መግለጫ÷ በ2016 በጀት ዓመት የክልሉን ምጣኔ ሃብታዊ እድገት 8 በመቶ ለማድረስ…

በጤፍ ምርት ላይ እሴት በመጨመር ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እሴት በመጨመር የጤፍ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል "አንድ ተመራጭ ምርት በአንድ ሀገር" የተሰኘ የሁለት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ። ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ መንግስት እና የዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት ትብብር የተዘጋጀ ነው።…

በክልሉ 272 ሺህ 994 ሄክታር መሬት ታርሶ ለዘር መዘጋጀቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተያዘው የመኸር ወቅት 272 ሺህ 994 ሄክታር መሬት ታርሶ ለዘር ዝግጁ እንደሆነ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ የግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ…