Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ወታደራዊ የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ ወታደራዊ የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ትብብራቸውን ለማሳደግ ተስማምተዋል። የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) ከላይቤሪያ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ብርጋዲየር ጄኔራል ጄራልዲን ጃኔት ጆርጅ ጋር በአዲስ አበባ…

ለአፍሪካ ሀገራት አርዓያ የሚሆነው የኢትዮጵያ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ …

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ ለአፍሪካ ሀገራት አርአያ የሚሆን ነው አሉ የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ፡፡ በላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ የተመራ ልዑክ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጎብኝት አድርጓል፡፡…

ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች ለመላው አፍሪካ ኩራት ናቸው – የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች ለመላው አፍሪካ ኩራት ናቸው አሉ የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ። በሚኒስትሯ ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክን ጎብኝቷል።…

ሰሜን ኮሪያ የክሩዝ እና ፀረ የጦር መርከብ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰሜን ኮሪያ ሁለት ስትራቴጂክ ክሩዝ ሚሳኤል እና ሶስት ፀረ የጦር መርከብ ሚሳኤል ሙከራ በተሳካ ሁኔታ አድርጋለች፡፡ የሚሳኤል ሙከራዎቹ ቾኢ ሂዮን ከተባለው የሰሜን ኮሪያ አውዳሚ የጦር መርከብ ባለፈው እሁድ የተካሄዱ መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡…

ሊቨርፑል ከፒኤስጂ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት መደረግ ይጀምራሉ፡፡ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ የፈረንሳዩን ክለብ ፒኤስጂን ያስተናግዳል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በፓርክ ደ ፕሪንስ ያደረጉትን የመጀመሪያ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ አቀባበል አደረጉ

‎አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ አቀባበል አድርገዋል። የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ…

አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ ወሽመጥ የሚገቡና የሚወጡ መርከቦችን ማገድ ጀመረች

‎አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ የባሕር ላይ ጉዞዎችን ማገድ መጀመሯን አስታውቃለች፡፡ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡና የሚወጡ መርከቦች ላይ በዛሬው ዕለት ክልከላ እንደሚጥሉ ይፋ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡…

የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት ዳግም ያረጋገጡ አዲስ የአርኪዮሎጂ ግኝቶች…

በኢትዮጵያ አፋር ስምጥ ሸለቆ በመካከለኛው አዋሽ የምርምር ፕሮጀክት ከ100 ሺህ ዓመታት በፊት ይኖሩ የነበሩ የጥንታዊ ሆሞ ሳፒየንስ ቅሪተ አካላት ተገኝተዋል አለ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን፡፡ የባለሥልጣኑ የአጥኚ ቡድን የሰው ልጅ የዝግመተ ለውጥ ጉዞንና ጥንታዊ የአኗኗር ዘይቤን የሚያሳዩ…

ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ፓስፖርት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ፓስፖርት ለዜጎች ተሰጥቷል አለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፡፡ የአገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እንዳሉት ÷ ተቋሙ በመደበኛና አስቸኳይ ፓስፖርት፣ የቪዛ እና…

በጎሮ ጉቱ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ሕይወት አለፈ

‎አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አልፏል። አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ሲጓዝ በነበረ ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡…