Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ የቱሪዝም ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኬኒያ የመጡ የቱሪዝም ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ። ቱሪዝም ኢትዮጵያ ያዘጋጀው ይህ ጉብኝት መነሻው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ሲሆን መዳረሻው ደግሞ ሀረር እንደሆነ ተጠቁሟል። …

ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛና ማታ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 54 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው በ3ኛ ዙር ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥ 428 ተማሪዎች ሴቶች ናቸው።…

ጠ/ሚ ዐቢይ በአዋሬ አካባቢ ያሳደሱትን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት አስረከቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዋሬ አካባቢ ያሳደሱትን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት በዛሬው እለት አስረከቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአምስት ሳምንታት በፊት ዓመታዊውን የቤት እድሳት መርኃ ግብር ማስጀመራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ…

ከማዕድናት እና ከከበሩ ድንጋዮች 682 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት አመት ከማዕድናት እና ከከበሩ ድንጋዮች 682 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህ ወቅት በበጀት አመቱ ማዕድናት እና የከበሩ ድንጋዮች 682 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ሚኒስትር…

የዴልታ ኮቪድ ታካሚዎች በእጥፍ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል – ጥናት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታንያ በስፋት ተሰራጭቶ ከነበረው የአልፋ ኮቪድ19 ቫይረስ ይልቅ በዴልታ ኮቪድ የታመሙ ታካሚዎች በእጥፍ እንክብካቤ እንደሚሹ በእንግሊዝ የተሰበሰበ መረጃ አመላከተ፡፡ ጥናቱ እንዳመላከተው አዲሱ ዴልታ ኮቪድ ከበድ ያለና ከዚህ በፊት ከነበረው…

በመተከል ዞን መስከረም ወር ለሚካሄደው ምርጫ ምቹ የፀጥታ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን መስከረም ወር በመተከል ዞን ለሚካሄደው ምርጫ ምቹ የፀጥታ ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን የዞኑ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ። የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስት ዋና ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ ከመከላከያ…

ህወሓት በላይ ጋይንት ያወደመው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተደረገለት ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በላይ ጋይንት ያወደመው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና እየተደረገለት መሆኑ ተገለጸ፡፡ ቡድኑ በነፋስ መውጫ የሚገኘውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጨምሮ በሌሎች የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን የሰሜን ምዕራብ…

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 132 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወራቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 132 ተማሪዎችን አስመረቀ። ከተመራቂዎቹ ውስጥም ወንድ 654 ሴት 478 ተማሪዎች ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት ከሰባት ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሳዑዲው ልዑል ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሳዑዲው ልዑል፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትር ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ ጋር በስልክ ተወያዩ። በውይይታቸው ወቅት በሁለትዮሽና የጋራ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የሳዑዲ ጋዜጣ ዘገባ…

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 5 ሺህ 726 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 726 ተማሪዎች አስመረቀ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ፥ በዋናው ግቢ ፣ በኦቶና ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል እንዲሁም በታርጫ ግቢ…