Fana: At a Speed of Life!

በግልገል በለስ ከተማ የከተራ በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተራ በዓል በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ይገኛል። በአከባበሩ ላይ ከተለያዩ አድባራት የተወጣጡ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው በመውጣት ወደ ባሕረ ጥምቀቱ እያመሩ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድሮች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ለጥምቀት በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በሀገር…

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ለከተራ እና ጥምቀት በዓላት ያስተላለፈው የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፡-

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ጥምቀት ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው የአደባባይ የወል በዓል ነው። በዓሉ ከሃይማኖታዊ በዓልነት ባሻገር የሚታይ ለዓለም በማይዳሰስ ቅርስነት የተበረከተ ሀብታችን ነው፡፡ የበዓሉ መሠረት ሃይማኖታዊ ነው፡፡…

መንግሥት ለጎንደር የሚሰስተው ነገር የለም – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግሥት ለጎንደር ከተማ የሚሰስተው ነገር የለም ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ከጎንደር ከተማ ነዋሪ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴን ጨምሮ የፌዴሽን ምክርቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ…

የከተራ በዓል በሐረር ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረር ከተማ የከተራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። ታቦታቱ ከመንበራቸው ተነስተው በህዝበ ክርስቲያኑ ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባህር በመጓዝ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በበዓሉ የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስን ጨምሮ…

በጅማ ከተማ የከተራ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ከተማ የከተራ በዓል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው፡፡ በአከባበሩ ላይ የጅማ፣ የየም እና የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጽኡ አቡነ እስጢፋኖስን ጨምሮ ካኅናት እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ተገኝተዋል፡፡ ከከተማው 16 ደብሮች የተውጣጡ…

በሻሸመኔ ከተማ የከተራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሻሸመኔ ከተማ የከተራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡ ታቦታት ከአራቱም የከተማዋ አቅጣጫዎች በካህናት እየተመሩ እና በሕዝበ ክርስቲያኑ ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባሕሩ እየተጓዙ ነው፡፡ በቢቂላ ቱፋ

ብልጽግና ፓርቲ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በትኩረት ይሰራል- አለሙ ስሜ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና ፓርቲ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠልና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ የብልጽግና ፓርቲ የፌዴራል ተቋማት አደረጃጀት ሰብሳቢና የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። የብልጽግና ፓርቲ…

በደሴ ከተማ የከተራ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ደሴ ከተማ የሚገኙ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው በመነሳት በምዕመናን፣ ዘማሪያንና ካህናት ታጅበው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ እያቀኑ ነው፡፡ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የተለያዩ አካላት ተቀናጅተው እየሠሩ ነው፡፡ በሙሉቀን አበበ

በአዲስ አበባ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው በመውጣት ወደ 66 ጊዜያዊ ማረፊያ ይወርዳሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ታቦታት ከመንበረ ክብራቸው በውጣት ወደ 66 ጊዜያዊ ማረፊያ እንደሚወርዱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የፕሮጀክቶች መምሪያ ኃላፊ መላከ ሕይዎት አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ ገለጹ። በአዲስ አበባ የጥምቀት በዓል በድምቀት…