Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በይፋ አስጀምረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ዞን አረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር ነው የመርሐ ግብሩን መጀመር ያበሰሩት፡፡ በዘንድሮው የአንድ…

በአረንጓዴ አሻራ ዓለምን የሚያስደምም ስራ እየሰራን ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዓለምን የሚያስደምም ስራ እየሰራን ነው አሉ፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡…

የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ከፍታ የማውጣት ጥሪ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ከፍታ የማውጣት ጥሪ ነው አለ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በሰጡት መግለጫ፥ የዘንድሮው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ…

በዛሬው ዕለት በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት 700 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመላ ሀገሪቱ የሚካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አስመልክተው ባስተላለፉት…

የአካባቢ ጥበቃ ስራ ውጤቱ በሂደት እየተገለጠ የሚሄድ ነው – የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት በአንድ ጀንበር 700 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል አለ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷…

የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን እያገኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን እያገኙ ነው አለ በኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢኒስቲትዩት። በኢኒስቲትዩቱ የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ከሰኔ ወር ጀምሮ…

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ለማህበራዊ መስተጋብር፣ ለኢኮኖሚ ፈጠራ እና ለዓለም አቀፍ ተሳትፎ ኃይል ሆኗል – ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ለማህበራዊ መስተጋብር፣ ለኢኮኖሚ ፈጠራ እና ለዓለም አቀፍ ተሳትፎ ኃይል ሆኗል አለ ብልጽግና ፓርቲ። ፓርቲው የአረንጓዴ አሻራን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ በመትከል ማንሰራራት እንደሚቻል አርአያ ሆና…

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ጅግጅጋ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በነገው ዕለት በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ጅግጅጋ ገብተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ የውብ ባህል ባለቤት፣…

በመኪና አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከደሴ ወደ ኮምቦልቻ ሲጓዝ የነበረ አይሱዚ መኪና በተለምዶ ሀረጎ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ በመገልበጡ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል። የመኪና መገልበጥ አደጋው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ የደረሰ መሆኑ ተገልጿል። የኮምቦልቻ ከተማ…

የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው የኢትዮያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቷል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከብሮድካስት እና ስም ስያሜ መብት የሚያገኙት ክፍፍል ይፋ አድርጓል።…