Browsing Category
ስፓርት
መቻል ስሑል ሽረን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ስሑል ሽረ በመቻል 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
የመቻልን ግቦች ሽመልስ በቀለ በ24ኛው እንዲሁም ግሩም ሀጎስ በ39ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የስሑል ሽረን የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ አስቻለው ታመነ በ53ኛው…
መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 ረትቷል፡፡
የማሸነፊያዋን ግብም አዎት ኪዳኔ በ82ኛው ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡
በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ…
ዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኙን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንግሊዙ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ጁለን ሎፕቴጌን ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ከኃላፊነታቸው ማሰናበቱ ተሰምቷል፡፡
ስፔናዊው የ58 አመት አሰልጣኝ የለንደኑን ክለብ በአሰልጣኝነት የተረከቡት ከዴቪድ ሞይስ ስንብት በኋላ…
ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህርዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ባህርዳር ከተማ በጄሮም ፍሊፕ ብቸኛ ጎል ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 ማሸነፍ…
ኢትዮጵያ መድን ስሑል ሽረን አሸንፏል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ መድን ስሑል ሽረን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡
መሐመድ አበራ፣ ረመዳን የሱፍ እና መስፍን ዋሼ የኢትዮጵያ መድን ጎሎችን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የስሑል ሽረን ግብ ያስቆጠረው ደግሞ አሌክስ ኪታታ…
አዳማ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡
በአዳማ ሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ÷ የአዳማ ከተማን ጎሎች አሜ መሐመድ፣ ነቢል ኑሪ እና ኤሊያስ ለገሠ አስቆጥረዋል፡፡…
ሊቨርፑል ታሪካዊ ተቀናቃኙ ማንቸስተር ዩናይትድን ዛሬ ይገጥማል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር መሪው ሊቨርፑል 14ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ማንቸስተር ዩናይትድን ዛሬ ምሽት በሜዳው አንፊልድ ሮድ ያስተናግዳል፡፡
ሊጉ በፈረንጆቹ 1992/93 የውድድር ዓመት በአዲስ መልክ ከተዋቀረ ጀምሮ…
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ክብረ ወሰን በመስበር አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ እና አትሌት ሩቲ አጋ በ2025 የሺያሚን የማራቶን ሩጫ ውድድር ሪከርድ በመስበር አሸንፈዋል፡፡
በዢያሜን ማራቶን 2025 የወንዶች ሩጫ ውድድር አትሌት ዳዊት ወልዴ 2:06:06 በሆነ ሰዓት በመግባት ቀደም ሲል…
ባሕርዳር ከተማና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ሙጂብ ቃሲም ባስቆጠራት ግብ እስከ ጨዋታው መጠናቀቂያ ድረስ…
ማንቼስተር ሲቲ በሰፊ የግብ ልዩነት ሲያሸንፍ ቼልሲ ነጥብ ጥሏል
አዲስ አበባ፣ ታህሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ማንቼስተር ሲቲ ዌስትሃም ዩናይትድን 4 ለ 1 ሲያሸንፍ ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ለማንቼስተር ሲቲ የማሸነፊያ ግቦቹን…