Fana: At a Speed of Life!

በሞጆና አዳማ ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን የኃይል መቆራረጥ የቀነሰ ሥራ መሰራቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞጆና አዳማ ከተሞች የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን የኃይል መቆራረጥ የቀነሰ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ሥራ መሰራቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዳማ ሪጅን አስታወቀ። በከተሞቹ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የሚቀርበውን የኃይል አቅርቦት…

አንጋፋው አርቲስት መርዓዊ ስጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ሰው መርዓዊ ሥጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ክላርኔት በመጫወት የሚታወቀው አርቲስት መርዓዊ፤ ከሙዚቀኛነቱ ባለፈ በትወና መድረክ ተወዳጅነትን ማትረፍ ችሏል፡፡ አርቲስት መርዓዊ ስጦት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ…

ለምግብነት መዋል የሌለበትን ጨው ሲያመርቱ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል ሀዋሳ እና ለኩ ከተሞች ለምግብነት መዋል የሌለበትን ጥሬ ጨው በድብቅ ሲያመርቱ እጅ ከፍንጅ የተያዙ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡ በህገወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩት ሸጋ፣ ሺማና ልዩ አዮዳይዝድ ጨው በሚል ህገወጥ የንግድ…

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሩሲያ-ዩክሬን የተኩስ አቁም ዙሪያ ከሩሲያ አቻቸው ጋር ይወያያሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ-ዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ዙሪያ በነገው ዕለት ከሩሲያው አቻቸው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚወያዩ አስታወቁ፡፡ በዚህ ሳምንት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው፤ ስለተኩስ አቁሙ ጥረት…

በ120 ሚሊየን ብር እየተገነቡ ካሉ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች መካከል ሥድስቱ ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል ገጠር ወረዳ በ120 ሚሊየን ብር እየተገነቡ ከሚገኙ 14 የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች መካከል ሥድስቱ ለአገልግሎት በቁ፡፡ የውኃ ፕሮጀክቱን ዛሬ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ናቸው።…

የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን 57ኛው አህጉራዊ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ ልማትና የፕላን ሚኒስትሮች ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በጉባዔው ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ…

ለሕብረተሰቡ ጥያቄዎች የተሰጠው ምላሽ በዚህ ሣምንት እንደሚቀርብ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕብረተሰቡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ላቀረባቸው ጥያቄዎች የተሰጠው ምላሽና ማብራሪያ በዚህ ሣምንት እንደሚቀርብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ባለፈው ሣምንት፤ በትምህርት፣ ጤና፣ ኢኮኖሚ ጉዳዮችና በሌሎች አምራች ዘርፎች ላይ…

“የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲካሄድ የቆየው የንግድ ትርኢት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 14ኛው "የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪ ሀሳብ ተሰናድቶ የቆየው የንግድ ትርኢት ተጠናቅቋል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የንግድ ትርኢቱ ሸማች እና አምራችን በቀጥታ ከማገናኘቱም ባሻገር የሀገራችንን እምቅ አቅም…

የተፈጥሮ ሀብት ልማትን መተግበር የብልጽግና ማረጋገጫ አንዱ መንገድ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአካባቢን ጸጋ ለይቶ፣ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃን በንቃት መተግበር የሀገር ብልጽግና ማረጋገጫ አንዱ መንገድ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት…

ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ‘ቁርዓን - የእውቀትና የሰላም ምንጭ’ በሚል መሪ ሐሳብ በሁለቱም ጾታዎች ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፉ የቁርዓን ሒፍዝ ውድድር ተጠናቀቀ፡፡ በዚሁ መሠረት በወንዶች ከኦሮሚያ ክልል ቃሪዕ ሳላሀዲን አብዱረህማን እንዲሁም በሴቶች ከአማራ ክልል ቃሪዕ…